የቅድመ መደበኛ መምህራንን አቅም መገንባት ወሳኝ ነው ተባለ

  • -

የቅድመ መደበኛ መምህራንን አቅም መገንባት ወሳኝ ነው ተባለ

Print Friendly, PDF & Email

 

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና ሥነ-ትምህርትና ሥነ ባህርይ ተቋም ከምስራቅ ጐጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር በደጀን ወረዳ ለሚገኙ 94 የቅድመ መደበኛ አመቻች መምህራን በደጀን ከተማ የ2 ቀን ስልጠና ሰጠ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት የስልጠናና ማማከር መኮንን አቶ ባሳዝነው ድረስ እንደገለፁት ለቅድመ መደበኛ አመቻቾች ስልጠና መስጠት አላማው ለመደበኛ ትምህርት ቁልፍ እና መሠረት የሆነውን የቅድመ መደበኛ ትምህርት በደጀን ወረዳ ምንም አይነት ስልጠና ሳያገኙ በልምድ እያስተማሩ ላሉ አመቻቾች ስለህፃናት አያያዝ፣ እንክብካቤ፣ ጤንነት እና የማስተማሪያ ዘዴን አውቀውት ህፃናትን በአግባቡ መንከባከብና መያዝ እንዲችሉ ለማድረግ እና የነበረባቸውን የክህሎት፣ ዕውቀትና አመለካከት ክፍተት መሙላት ለማስቻል ነው፡፡ ስልጠናው በሥነ ትምህርትና ስነ ባህሪ ተቋም መምህራን ዶ/ር ተሰራ ቢተው፣ ዶ/ር አባትሁን አለኸኝ እና ዶ/ር ውሃቢ ብርሃኑ ተሰጥቷል፡፡

በምስራቅ ጐጃም ዞን በተደረገው የፍላጐት ደሳሳ ጥናት በአብዛኛው የቅድመ መደበኛ አመቻች መምህራን ህፃናትን የሚያስተምሩት ባላቸው ልምድ እንደሆነና ስልጠና እንደሚያስፈልጋቸው በማረጋገጥ ከህፃንነት ጊዜ ጀምሮ እስከ መዳበር ምንነት፣ የልጆችን ባህርይ ምን እንደሚመስልና ምን እንደሚፈልጉ፣ የማስተማሪያ ስነ-ዘዴው ምን መምሰል እንዳለበት፣ ለህፃናት የጨዋታ አስፈላጊነት፣ ከወላጅ ጋር የሚኖረው ተግባቦት ምን መሆን እንዳለበት፣ ጤንነታቸውን እንዴት መከታተል እንደሚችሉ፣ የልጆች የአስተዳደግ ዘይቤዎችን፣ እና የመሳሰሉትን በተመለከተ ስልጠና መስጠት እንዳስቻላቸው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ትምህርትና ሥነ ባህርይ ተቋም የሥነ-ባህርይ መምህር ዶ/ር ውሃቤ ብርሃኑ አብራርተዋል፡፡

የምስራቅ ጐጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የቅድመ መደበኛ ፎካል ፐርሰን አቶ ዮሐንስ ሰውነት በበኩላቸው ሰልጣኞች /አመቻቾች/ ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው የነበረባቸውን ክፍተት በመሙላት ህፃናትን በአግባቡ በመያዝ፣ በመንከባከብና በማስተማር ለመደበኛ ትምህርት ብቁ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲችሉ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ድጋፍ የመስጠቱን ስራ በማጠናከር እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

ሰልጣኝ መምህራንም የተሰጣቸው ስልጠና ጥሩ፣ ገንቢ እና ተገቢነት ያለው እንደሆነና ከስልጠናው ባገኙት ግብዓት ለወደፊት ህፃናትን በጥሩ ሁኔታ መንከባከብና ማስተማር እንደሚችሉ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

    • AAU

DMU Radio Broadcasting . . .