የታላቁን ህዳሴ ግድብ ከደለል ለመታደግ የአካባቢን ብዝሃ ህይወት መጠበቅ አስፈላጊ ነው ተባለ፡፡

  • -

የታላቁን ህዳሴ ግድብ ከደለል ለመታደግ የአካባቢን ብዝሃ ህይወት መጠበቅ አስፈላጊ ነው ተባለ፡፡

Print Friendly, PDF & Email

 

(ደማዩ ነሀሴ 27/2013 ዓ.ም )፡-የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ የአካባቢ ደን ምርምር ተቋም ጋር በመተባበር አባይ ሸለቆ ውስጥ ኩራር ቀበሌ የቆላ ቅርቀሃ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄደ፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙሉቀን አድማሱ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው እንደተናገሩት ደጀን ወረዳ ኩራር ቀበሌ ሃጅ ችግኝ ጣቢያ አካባቢ  የቆላ ቅርቀሃ ተከላ ከሁለት ወር በፊት ወደ ስራ የተገባ ሁኔታ ቢሆንም ስራው ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ አስፈላጊ በመሆኑ ወደፊት ሰብሉ ሲነሳ ልቅ ግጦሽ ስለሚሆንና ችግኙ ጥበቃ ስለሚያስፈልገው ለአርሶ አደሮች የሙያ እገዛ እንዲደረግልን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

 የኢፌዲሪ አካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ አካባቢ ደን ምርምር ኢንስቲቲዩት፣ እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣ ብዙሃሕይወት ለመጠበቅ የአራትዮሽ ስምምነት አድርገዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ በበኩላቸው  ይህን ፕሮጀክት በጋራ መሬት ላይ ለማውረድና ሀገርን እንደ ሀገር ለመቀየር በተለይ ደግሞ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ከደለል ለመታደግ ለአርሶ አደሩ ደግሞ የኑሮ መሰረት የሆነው ነገር በዘላቂነት የአካባቢው ብዙሃሕይወት ለመጠበቅ ከመጀመሪያ ጀምሮ የአባይን ጎርጅ ጨምሮ አጠቃላይ  ብዝሃ ህይወቱንና የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተሻለ መንገድ እንታደጋለን በሚል የኢትዮጵያ አካባቢና ደን ምርምር ኢስቲቲዩትና የኢፊዲሪ አካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣  ይህን ሃሳብ ይዘው ስለመጡ  በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና በማኔጅመንቱ ስም ታላቅ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ  ብለዋል፡፡

ዶክተር ታፈረ መላኩ አክለውም ቻይናና ሌሎች ትልልቅ ሃገራት  በተለይ የምስራቁ አል ሀገራት አብዛኛው የፋብሪካ ውጤታቸው በቅርቀሃ ምርት የተመሰረተ ነው  ቢሆንም እንደ ሀገር ቢታሰብ በሙሉ ዙሪያውን የአባይ ጎርጅ ጎጃምን ይዞራልና የአባይን ጎርጅ ብንተክለው ሀገራችን በዚህ ብቻ የውጭ ምንዛሪ ታስቀራለች ሌላው ብዛ ህይወቱ ይቀየራል የምናየው ምድረ በዳ አረንጓዴ ይሆናል ከዛ ባለፈ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ከደለል መታደግ ይቻላል ለብዙ አመት ለትውልድ የሚተላለፍ ይሆናል እናም ዘርፈ ብዙ ጥቅምና ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ  አለው በማለት  ተናግረዋል፡፡

 የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፊሰር ደምሳቸው ሽታው  እንዳሉት ፕሮጀክቱ አባይ በረሃ ውስጥ ስራ የጀመረው ሰኔ 27/10/2013 ዓ.ም ሲሆን ስልሳ ስምንት ሽህ አራት መቶ ስልሳ ሶስት የቅርቀሃ ችግኝ ጣቢያው ውስጥ ተዘጋጅቶ ከዚህ ውስጥ  ስልሳ ስድስት ሽህ  የቅርቀሃ ችግኝ ተተክሏል፡፡

 ዛሬ ደግሞ  አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ አስር ችግኞች ውስጥ ወደ ሰባት መቶ የሚደርሱ ችግኞችን በማጠቃለያ ፕሮግራም ይተከላል፡፡ ይህ ሆኖ እርከን ጠብቀን በአርሶ አደር ማሳ ላይና ሩፋኤልና ገብርኤል ቤተክርስትያን የተተከለ ቢሆንም እስካሁን ድረስ 156.2 ሄክታር መሬት በቅርቀሃ ችግኝ ተሸፍኖአል፡፡ በዚህ ሂደት ያጋጠሙን ችግሮች በዋናነት የክፍያ መዘግየት ለአርሶ አደሮች፣ ለሹፌሮች፣ ለወረዳ ግብርና ባለሙያዎች፣ ሆኖ ዶ/ር አጌና ኢንጁሎ  የሰጡት አቅጣጫ  አርሶ አደሩ በራሱ ማሳ ላይ እንዲተክል የሚል ሀሳብ ነበር ነገር ግን መረጃው  ዘግይቶ የደረሰ ስለሆነና መጀመሪያ የጋራ ቦታ ነበር የፈለግነው ስለሆነም ያገኘናቸውን ቦታዎች ካየ በኋላ ከዚህ ይልቅ  የአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ቢሆን የተሻለ  ይሆናል  የሚል አቅጣጫ ተሰጦ  በአጭር  ጊዜ ውስጥ  አርሶ አደሩን አሳምኖ ወደ ስራ ማስገባት ስለሚጠይቅ ለዚህ ደግሞ ግብርና ኮሌጅ፣ ዞን አካባቢ ጥበቃ፣ እገዛ አድርገውልናል::

የኢትዮጵያ አካባቢናደን ምርምር ኢስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር  ዶ/ር አጌና አንጁሎ እንደገለጹት ይህ ሳይት አጠቃላይ የዚህ የተፋሰሱ አንድ አካል ቢሆንም የዚህ ተፋሰስ ላይ የቆላ ቅርቀሃ ችግኝ አፍልተን ለተከላ ያሳሰበን ሁልጊዜ የምንሰራው ስራ አለ ነገርግን  ለየት አድርገን በጥናትና ውጤታማ በሆነ መልኩ መስራት አለብን ብለዋል፡፡ አርሶ አደሩ ይህ አካባቢ በጣም ተዳፋት የሆነ መሬት ስለሆነ ለችግሩና ኑሮውን ለመቋቋም ሲል አካባቢውን መንጥሮ ወደ እርሻ ገብቷል ይሁን እንጅ እርሻው ላይ በእየ እርከኑ ዛፍ ቢኖር ስነ ምህዳሩን ይጠብቃል እንዲሁም ምርትም እንደሚያገኝበት ከማሰብ አንጻር ምን አይነት የዛፍ ዝርያ ይሻላል የሚለውን ስናስብ የኢስቲቲዩቱ የምርምር ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች ተነጋግረን የቆላ ቅርቀሃ ቢሆን የአካባቢውን ስነምህዳር ይቋቋማል ይህ ደረቃማ አካባቢ ስለሆነ ለህብረተሰቡም ደግሞ ከአራት አመት በኋላ ምርት ያገኝበታል ስለዚህ አርሶ አደሩም መኖ ያገኛል ሁለተኛ ደግሞ እያንዳንዱ አርሶ አደር ላይ ያለ ቅርቀሃ  እየታጨደ ለገበያ ይውላል ብለው  ሌላው  የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ፣ እንዲሁም የምርምርና ማህበረሰብ ዘርፍ ይህን ሃሳብ አንስተን ስንወያይ በጣም ደስተኞች  ከመሆናቸው አልፈው  ሃሳቡን ተቀብለው ወደ መሬት ለማውረድ ገንዘብ ያስፈልጋል  የኢፌዲሪ የአካባቢ ደንናየአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ገንዘብ ከሚያገኘው የተለያየ ሃብት ለዚህ ስራ መድቦ አራቱም ተቋማት በመፈራረም  ወደስራ እንደተገባ ተናግረዋል፡፡        


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .