የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ  የአዲስ አመት መልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል። 

  • -

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ  የአዲስ አመት መልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል። 

Print Friendly, PDF & Email
 
 
የመልካም ምኞቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። 
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ለመላው የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ (መምህራን፣የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች) አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤና፣ የበረከትና የስኬት ዘመን እንዲሆንላችሁ ከልቤ እመኛለሁ።  
 
ለተቋማችን፣ ለሕዝባችንና ለሀገራችንም ዘመኑ የሠላም ፣የጤናና የብልጽግና እዲሆንልን አመኛለሁ። ዘረኞች፣ ባንዳዎችና ከሃዲዎች  ሲጸነሱ ጀምሮ ኢትዮጵያዊያንን በዘር፣ በሀይማኖትና በመንደር በመከፋፈል ፍዳና መከራቸውን ቢያበዙትም በመቃብራቸው አፋፍና ዋዜማ ላይ መልሰው ኢትዮጵያዊያን አንድ ስላደረጓቸው የኢትዮጵያ ትንሣኤ በቅርብ እውን እንደሚሆን እምነቴ የጸና ነው።
 
 ሥለሆነም አሁን የተፈጠረው ሀገራዊ አንድነትና ሀገራዊ ፍቅር ሁሉም ወጣቶቻችን በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪዋች የራሳቸው ውርስ እንዲያደረጉት ከመቸውም ጊዜ በላይ ተግተን ልንሠራ ይገባል። 
 
ሕዝባችንና ሀገራችን ከገጠማቸው ፈተና በአጭር ጊዜ እንዲወጡ የጀመርነውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክረን እንድንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
 
 ዩኒቨርስቲ ያችን በአዲሱ ዓመት የተሻለ ስኬት እንዲያስመዘግብ ሁላችንም ከመቸውም ጊዜ በላይ በጋራ እንድንረባረብ ጥሪዬን አቀርባለሁ። 
 
                   መልካም በዓል!
                  ታፈረ  መላኩ(ዶ/ር)
                          ፕሬዚዳንት    
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
 
 
 

Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .