ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና የኢ.ፊ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ቁልፍ የስራ የአፈጻጸም ስምምነት ውል (Performance Contracting Agreement) ተፈራረሙ።

  • -

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና የኢ.ፊ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ቁልፍ የስራ የአፈጻጸም ስምምነት ውል (Performance Contracting Agreement) ተፈራረሙ።

Print Friendly, PDF & Email

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትን፤ የማህበረሰብ አገልግሎት ተደራሽነት እና አግባብነትን መሰረት ያደረገ ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (KPIS) ስምምነት ውል (Performance Contracting Agreement) በዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ሳይህ ካሰው (ዶ/ር) ከኢ.ፊ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርመዋል።

ይህ የውል ስምምነት መሰረት ያደረገባቸው ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲያችን ተግባራዊ እየተደረጉ የቆዩ ሲሆን በቀጣይም በስምምነቱ መሰረት ስራዎችን በየደረጃው ላሉ የስራ ክፍሎች እና ሰራተኞች በማውረድና ትኩረት ተሰጥቶ ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት የሚሰራ መሆኑን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በውል ፊርማ ፕሮግራሙ ላይ አረጋግጠዋል።

የቁልፍ ስራዎች አፈጻጸም ውል (Performance Contracting Agreement) ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይንሳዊና ዓለም አቀፋዊ መለኪያዎች ላይ ያተኮረ ዕድገት እንዲኖራቸው የሚያደርጋቸው ሲሆን ስምምነቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የክትትልና ግምገማ ስርዓት እንዲኖርና ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኳቸው ላይ አትኩረው እንዲሰሩ በኢ.ፊ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ተገልጿል።

የኢ.ፊ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የአፈጻጸም ስምምነት ውል በተፈራረሙበት ወቅት የኢ.ፊ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴርን በመወከል ውሉን የተፈራረሙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ናቸው።


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .