ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የክረምት ትምህርት መርሃ-ግብር በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት እየተካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

  • -

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የክረምት ትምህርት መርሃ-ግብር በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት እየተካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

Print Friendly, PDF & Email

እንደሚታወቀው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በክረምት ትምህርት  መርሃ-ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑ ይታወቃል ይሁን እንጅ አሁን በአገራችን በተፈጠረው ሁኔታ አብዛኛዎቹ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መርሃ-ግብሩን ለማቆም ሲገደዱ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግን የክረምት ትምህርት በወጣለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እየተከታተሉ እንደሚገኙ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አያሌው ሲሳይ ገልፀዋል፡፡ 

                                 ዶ/ር አያሌው ሲሳይ                                        

አገሪቱ በአሁኑ ወቅት በእናት ጡት ነካሾች የህልውና አደጋ እንደተጋረጠባት  ይታወቃል  ነገር ግን የትምህርት መርሃ-ግብሩ ሳይቋረጥ ጎን ለጎን የሀገር ህልዉና የማስከበር ዘመቻ ላይ ሀገራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መማር ማስተማሩን እያካሄደ ነው ብለዋል፡፡ 

ዩኒቨርሲቲው በሁሉም የትምህርት መስኮች  በክረምቱ መርሃ-ግብር አስራ አንድ ሺህ  አምስት መቶ ሰባ ስምንት ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡ የዘንድሮውን መርሃ-ግብር የሚለየው ሀገሪቱ ህልዉና  አደጋ ላይ በወደቀችበት ወቅት መሆኑ  ተማሪዎቹ በቁጭት በተደበላለቀ ስሜት የትምህርት መርሃ-ግብሩ መካሄዱ ተጽኖ ቢፈጥርም ዝም ብለን እጅግራችንን አጥፈን አልተቀመጥንም እየሰራን ማገዝ በምንችለው ሁሉ በሀገሪቱና በማንነታችን የመጡብንን የውስጥና የውጭ ጠላቶችን ድባቅ የምንመታበትና የሀገሪቱን ህልዉና የምናስቀጥልበት ወቅት እንዲሁም አገራችን የገጠማት አሁናዊ ከባድ ተግዳሮት፣በስነልቦና ሳንጎዳ፣ ሳንረበሽ ሁላችንም  ወታደር፣ መምህር፣ነጋዴ፣ መሆን አንችልም ስለሆነም እያንዳንዳችን በተሰማራንበት ሙያ ጠንክረን ሰርተን  በጦር ግንባር ላይ እየተፋለመ ላለው መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ሃይል፣ ለሚሊሽያ አባላት  ደመወዛችንና ሎጀስቲክ ድጋፍ ማድረግ ይኖርብናል ብለው ተናግረዋል፡፡      

ተማሪ አምሳሉ ህልምነህ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሳይንስና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ የእንግሊዝኛ ትምህርት ክፍል የስድስተኛ አመት ተማሪ  አምሳሉ ህልምነህ በበኩሉ  የመማር ማስተማሩ ሂደት ካለው ሀገራዊ ሁኔታጋር ተያይዞ ተጽኖ ቢያሳድርባቸውም የዩኒቨርሲተዉ አመራሮችና ማህበረሰብ ያለውን ሀገራዊ ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት እገዛ እየተደረገላቸው እንደሚገኝና የመማር ማስተማሩ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ይህንን ተቋቁመው  ግን ያለው ሀገራዊ ሁኔታ ተማሪዎችም ለመማር መምህራንም ለማስተማር ፈታኝ ቢሆንም ይህንን ተቋቁሞ በጥሩ ሁኔታ መማር ማስተማር ሂደት እየተካሄደ እንደሆነ ከአሁን በፊት በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት ለማከካስና መርሃ ግብሩን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲያልቅ መምህራኖቻቸው ጥረት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተማሪ ባንቴ ሞላ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሳይንስና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ የስነ ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ክፍል የሶስተኛ አመት ተማሪ ባንቴ ሞላ እንደገለጸው  የክረምት ትምህርት መማር ማስተማሩ ጥሩ ሁኔታ ላይ ቢሆንም አገራዊ ጉዳይ ትህነግ( ህውሃት)  በፈጠረው አማራን የማጥፋት የውክልና ጦርነት  አገራችን ችግር ውስጥ ናት ስለሆነም እኛ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን  ሰላም የማስጠበቅ ሃላፊነት ይኖርብናል ብሏል ፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .