ሀገርን ለመገንባት ከትምህርት ባሻገር በስነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ ያስፈልጋል ተባለ

  • -

ሀገርን ለመገንባት ከትምህርት ባሻገር በስነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ ያስፈልጋል ተባለ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደ/ማ/ዩ፡- የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ለአዲስ ገቢና ለተመራቂ ተማሪዎች የአዘጋጀዉን የስነ-ምግባር ስልጠና ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች 10/11/2013ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች ደግሞ 13/11/2013 ዓ.ም በደራሲ ሃዲስ አለማየሁ የጉባኤ አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናዉን በጋራ የሰጡት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ይበልጣል ደምሰዉና በስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ክፍል የፖለቲካል ሳይንስ መምህር  ዶክተር መኮነን አለኸኝ ናቸዉ፡፡

የስልጠናዉን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ይበልጣል ደምሰዉ በንግግራቸዉ የዚህ ስልጠና ዓላማ  እንደ ሀገር መልካም ምግባርና ጠንካራ የሞራል እሴትን ለመገንባት ነዉ ብለዋል፡፡

በስልጠናዉ ከተነሱ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ዩኒቨርሲቲ መሆኑ፣ ደብረ ማርቆስ ከተማና አካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ስሜት የሚንፀባረቅበት አካባቢ መሆኑ፣ በአብዛኛዉ ሰዎች ወደ ሙስና የሚገቡበት መሰረታዊ ምክነያት የስነ-ምግባር ብልሹነት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የስነ-መግባርና  ግብረገብ ትምህርት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊሰጥ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ለፍቅርና ግብረገብነት ተግቶ መስራት፣ የፈጠራና የምርምር ችሎታን ማዳበር፣ ሙስናን የሚጸየፍና የሚዋጋ ትዉልድ መፍጠር፣ መስና ልማድ እንዳይሆን መስራት ትዉልዱ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ሌላዉ በስልጠናዉ የተነሳዉ አሁን በሀገሪቱ በስፋት እየተስታዋለ ያለ የሙስና አይነት ከባድ ሙስና ሲሆን ሀገሪቱ ያላትን የመልማት ዕድል እያጨለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አንድ ሰዉ በሙስና ሊዘፈቅ የሚችልበትን ሁኔታዎች የተጠቆመ ሲሆን የስራ ዕድል አለመኖር፣ጤናማ የሆነ የስራ ዉድድር መንፈስ አለመኖር ነዉ ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በሀገር ደረጃ ሙስና  ፓለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተጽኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡ ዛሬ ሀገሪቱ ለገባችበት ቀዉስ ዋነኛዉ  ምክንያት ሙስና ነዉ ብለዋል፡፡

“እንደ ሀገር ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በስነ-ምግባርና እና ግብረገብ ላይ ራሱን የቻለ ስርዓተ -ትምህርት በመቅረጽ ከታች ጀምሮ ህጻናትን በስነ-ምግባርና ግብረገብ ትምህርት ኮትኮቶ በማሳደግ ሙስናን መከላከል ይቻላል” ብለዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .