ለአዲስ ቅጥር መምህራን ስልጠና /Induction Training/ ተሰጠ

  • -

ለአዲስ ቅጥር መምህራን ስልጠና /Induction Training/ ተሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሰው ሀብት ልማት ስልጠና የስራ ክፍል አስተባባሪነት በዩኒቨርሲቲው አዲስ ለተቀጠሩ 34 መምህራን ከጥቅምት 14-17/2010 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡

የስልጠናው አስተበባሪ የሆኑት አቶ መላኩ ጥላሁን እንደገለጹት በቅጥር ወይም በዝውውር ምክንያት ዩኒቨርሲቲውን በአዲስ ለሚቀላቀሉ መምህራን የስራ ትውውቅ ስልጠና በየአመቱ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ወቅት ለአዲስ መምህራን የተሰጠው ስልጠናም የዚህ አካል ሲሆን ዩኒቨርሲቲውን በአዲስ የተቀላቀሉት መምህራን ለመማር ማስተማሩ ስራ አዲስ እንዳይሆኑ እና ለዩኒቨርሲቲው ራዕይና ተልዕኮ መሳካት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዲችሉ የስራ ትውውቅ ስልጠና/ Induction Training/ በመስጠት ወደ ስራ ማስገባት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የስልጠና ዋና አላማ የመምህራንን አቅም በማሳደግ የመማር ማስተማሩን ስራ ውጤታማ በሆነ መልኩ ማከናወን እንዲችሉ ማድረግ በመሆኑ የምዘናና ግምገማ  ስርዓት፤የክፍል አያያዝ፤ አሳታፊ የማስተማር ስነ ዘዴ፤ የዩኒቨርሲቲው ህግና ደንቦች እንዲሁም ስርዓተ-ፆታና ኤች አይቪ/ ኤድስ የሚሉ ርዕሶችን ያካተተ ስልጠና እንደተሰጠ ለማወቅ ተችሏል፡፡በቀጣይም ሌሎች ስልጠናዎችን በማዘጋጀት መምህራንን ማብቃትና አቅማቸውን የማጎልበት ስራ የሚሰራ መሆኑን አስተባባሪዉ አክለዉ ገልፀዋል፡፡

አስተያየት የሰጡት የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና በተደራጀና አሳታፊ በሆነ መልኩ የተሰጠ ስለሆነ በጣም ጥሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ልምድ የሌላቸዉ መምህራን ልምድ ካላቸው መምህራን ልምድ ማግኘት በማግኘታቸዉ ወደፊት በስራቸዉ ላይ በመተግበር የተማሪዎችን ዕውቀት፤ ክህሎትና አመለካከት ማሳደግ እንደሚችሉ ገለፀዋል፡፡

 


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .