በምርምርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የሴት መምህራንን ሚና ለማሳደግ ወርክሾፕ ተካሄደ

  • -

በምርምርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የሴት መምህራንን ሚና ለማሳደግ ወርክሾፕ ተካሄደ

Print Friendly, PDF & Email

 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት አስተባባሪነት በምርምርና ቴክኖሎጅ ፈጠራ ላይ የሴት መምህራንን ሚና ለማሳደግ ወርክሾፕ ተካሔደ፡፡

በወርክሾፑ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የውልሠው መላክ እንደገለፁት ወርክሾፑ ዓላማው የሴት መምህራንን የምርምርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ማሳደግ ነው፡፡ ሴት መምህራን ውስጣቸው ያለውን እምቅ ችሎታ አውጥተው ወደ ተግባር መቀየር እንዲችሉና ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት አርአያ ለሚሆኑ ሴት ተመራማሪዎች ስልጠና መስጠት አንደኛው ዘዴ ነው፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የዘር አዳቃይ ባለሙያና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ፈቲን ዓባይ ናቸው፡፡ ፕ/ር ፈቲን ሴት መምህራን ጥናትና ምርምር ከማድረግ አንፃር ክፍተት ስላለባቸው የራሳቸውን ተሞክሮ በመናገር የተነሳሽነት ስሜት በመፍጠር ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ መንገድ ማሳየት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ፕ/ር ፈቲን ተስፋ ባለመቁረጥ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ምርምር በመስራት አርሶ አደሩን የሥራቸው ጓደኛ በማድረግ በእችላለሁ መንፈስ ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም አምስት የምርጥ ዘር ዓይነቶችን በምርምር በማግኘት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደቻሉ በንግግራቸው ገልፀዋል፡፡ ፕሮፌሰሯ አያይዘውም በአሁኑ ሰዓት ግማሽ የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ሴቶች በመሆናቸው ይህንን ኃይል ያላሳተፈ ማንኛውም ልማት ውጤታማ ስለማይሆን ሴቶች ሁልጊዜ ዓላማና ራዕይ ይዘው ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ፕ/ር ፈቲን ሴት መምህራን ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ሲመክሩ፤ በራስ መተማመን ባህሪን ማዳበር፣ በሃላፊነት ለመስራት ፈቃደኛ መሆንና መሳተፍ፣ ዓላማ አስቀምጦ መስራትና ቆራጥ እርምጃ መውሰድ፣ የባለቤትን ድጋፍ ማግኘት፣ ደፋር፣ ትጉና ታታሪ መሆን፣ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም ሙያን ለማዳበር መትጋትና የተፎካካሪነት ስሜት ማሳደግ ሁሉም ሴቶች ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡ በምርምርና በሌሎች ተግባራት ውጤታማና ስኬታማ በመሆን ዕውቅናን ማግኘት እንደሚቻል በመግለፅ ሴቶች ውስጣቸው ያለውን ዕምቅ ችሎታ ማውጣት እንዲችሉ የሚሠጣቸውን ዕድሎች በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው በመግለፅ ፕ/ር ፈቲን ልምዳቸውን አጋርተዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .