በሶስት የግብርና ምርት ውጤቶች ላይ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚደረግበትን አሰራርና የህግ ማዕቀፎች በሚመለከት ለባለድርሻ  አካላት ስልጠና ተሰጠ

  • -

በሶስት የግብርና ምርት ውጤቶች ላይ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚደረግበትን አሰራርና የህግ ማዕቀፎች በሚመለከት ለባለድርሻ  አካላት ስልጠና ተሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የግብርና ምርቶችና ተያያዥ  የምርምር ውጤቶች ላይ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚደርግበትን አሰራር በተመለከተ ለባለድርሻ አካላት ህዳር 15/2015 ዓ.ም ከኢትዮጵያ የእምዕሮ ጥበቃ ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጧል።

የስልጠናውን ዓላማ በተመለከተ የደበረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ አጭር መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸው እንደገለፁት ጎጃም የሚታወቅባቸው የማር፣ የጤፍ እና የቅቤ ምርቶችን የንግድ ምልክት ለማሰጠት ዩኒቨርስቲያችን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ወደስራ የገባ መሆኑን ገልፀዋል። ጎጃም  የአምዕራዊ ንብረቶች ባለቤት ቢሆንም  በዚህ መስክ  የታሰበዉን ያህል ባለመሰራቱ  ብዛት ያላቸው በአእምዕሮ ጥበቃ ስር መሆን የሚገባቸው ዕዉቀቶች ባክነው ቀርተዋል።  እነዚህን እውቀቶች በማዳበርና በማሸሻል በአካባቢው በይበልጥ  በሶስቱ ምርቶች ትኩረት በማድረግ ወደ ስራ በመግባት ላይ ነን ብለዋል። አክለውም እንደገለፁት የሚመረቱ ምርቶች የንግድ ምልክት  (Trade Mark) እንዲኖራቸው ቢደረጉ አርሶ አደሮችን የተሻለ ምርት እንዲያመርቱ ያነቃቃቸዋል፤ በመሆኑም ሁሉም የተጣለበትን ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በማሳሰብ ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is patent2.jpg

የአእምሯዊ ንብረት ምንነትና  የሀገራችንን የሕግ ማዕቀፎች በሚል ርዕስ የአእምሯዊ ንብረት እሴት ልማት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ወርቁ  ስልጠና የሰጡ ሲሆን በስልጣናቸው ሶስት ሃሳቦችን ያነሱ ሲሆን እነሱም አእምሯዊ ንብረት ምንነት፣ አስተዳደርና የሕግ ማዕቀፎች ናቸዉ። የኢትዮጵያ የአእምሮ ጥበቃ ባለስልጣን ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የንግድ ምልክት ለማስመዝገብ  መከናወን ያለባቸው ተግባራት በመለየት ለንግድ ምልክት ፈላጊ አካላት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት ስለሆነ፤ የዛሬውም ስልጠና የጎጃም ምርቶችን የንግድ ምልክት ለማሰጠት ተቋሙ ከሚሰራቸው  ስራዎች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ልዪ ጣዕም ጥራት ያላቸውና የግብርና ምርቶችን የገቢያ ተወዳዳሪነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት  ለማሳደግ የእእምሯዊ ንብረት ምርቶችን ከምርቶች በቀላሉ ለመለየት እንደሚያስችል ጠቅሰዋል። በም/ስ/ጎጃም ዞን የሚመረቱ ምርቶችን የንግድ ምልክት ለማስመዝገብ መከናወን ያለባቸውን ተግባራት በተመለከተም አቶ ታደሰ ወርቁ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የሚመዘገበው ምርት በብዛትና በጥራት ለአካባቢው መለያ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በስልጠናው በተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም  ጠንከር ያሉ ሃሳቦች ተነስተዋል። ከተነሱት ሀሳቦችም መካከል  የምርት ጥራት፣ ብዛት የገበያ ትስስር ፣ የህብረት ስራ አደረጃጀቶች ያላቸው ፉይዳ፣ የንግድ ምልክቱ ይዞት የሚመጣው ጥቅምች ላይ ሰፊ ወይይት ተደርጓል።

This image has an empty alt attribute; its file name is patent3.jpg

በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የፖተንት ምርመራ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ በኃይሉ መልከጼዴቅ ለምዝገባ የሚቀርቡ የፈጠራ ስራዎች የፓተንት ማመልከቻ አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

በስልጠናው በቀረቡት ጽሁፎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለወደፊት በጋራ ለመስራት እንዲሁም የንግድ ምልክት ምዝገባው ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ ተደርሷል።


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .