በቡሬ ካምፓስ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

  • -

በቡሬ ካምፓስ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በቡሬ ካምፓስ በ2010 ዓ.ም ትምህርታቸውን ለመከታተል ተመድበው ለገቡ 500 አካባቢ አዲስ ተማሪዎች የሁለት ቀን የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡

የህይወት ክህሎት ስልጠናውን የሰጡት አሰልጣኝ መምህራን እንደገለፁት ስልጠናው ለሁሉም የግቢው ማህበረሰብ መሰጠት ያለበት ቢሆንም የጊዜ እና የስልጠና ቦታ እጥረት በመኖሩ በዚህ አመት ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል ለመጡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ብቻ እንዲሰጥ ተደርጓል ብለዋል፡፡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ በመሆኑ የተለያዩ የአኗኗር፤ ባህሪያት እና አመለካከት ችግሮች ስለሚገጥሟቸው እንዲሁም ከዚህ በፊት በቤተሰቦቻቸው ኃላፊነት ሲመሩ ከቆዩ በኋላ ወደ ግቢ ሲመጡ ራሳቸውን ችለው መኖርና መምራት ሲጀምሩ ልዩ ልዩ ችግሮች ስለሚገጥማቸው የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት የሚገጥሟቸውን ችግሮች በመቋቋም ሳይንሳዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ፤ የራስ መተማመን መንፈስ በተሞላበትና በተረጋጋ መንፈስ ውሳኔ በማሳለፍ የመጡበትን አላማ ለማሳካት እንዲችሉ ለማድረግ ስላስፈለገነው በማለት ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የዚህ ስልጠና ፋይዳ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው አሉታዊ የአቻ ግፊትን በመቋቋም ጠቃሚና ጎጅ ባህሪያትንና ድርጊቶችን በመለየትና በመቋቋም ውጤታማ ሆነው እንዲወጡ ያስችላቸዋል በማለት አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም በአጭር ጊዜም ቢሆን መሰረታዊ የሆነውን የህይወት ክህሎት ስልጠና መስጠት ተችሏል ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የተካፈሉ ተማሪዎች በበኩላቸው የዚህ አይነት ስልጠና መሰጠቱ ከቤተሰብና አካባቢያችን ተለይተን ግቢ ስንገባ ከዚህ በፊት ያልለመድናቸው በርካታ አዲስ የሆኑ ባህሪያት እና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ደባል ሱስ፤ ጊዜን ማባከን፤ የአቻን ግፊት አለመቋቋም፤ ራስን ማስጨነቅና መሰል ችግሮች ሊያጋጥሙን ስለሚችሉ ከማናቸውም አሉታዊ የአቻ ግፊት ነፃ ሆነን መቋቋም እንድንችል እና በራስ መተማመን መንፈሳችንን በማሳደግ የመጣንበትን አላማ ለማሳካት ያገለግለናል፡፡ በተለይም ደግሞ ሴት ተማሪዎች ለፆታዊ ትንኮሳ እና አቻ ግፊት ከወንዶች የበለጠ ተጋላጭ ስለሆንን ከዚህ ችግር ራሳችንን መጠበቅ ያስችለናል በማለት ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በዚህ ስልጠና ብቻ ሁሉንም ችግሮቻችን መቅረፍ ስለማይቻል የስርዓተ ፆታ እና መሰል ክበባት ተቋቁመው ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራው እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ የሴቶች፤ ኤች አይቪ/ኤድስና አካል ጉዳተኞች አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ አዘበብ በላይ የህይወት ክህሎት ስልጠናው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች መሰጠቱ የተማሪዎችን በራስ መተማመን መንፈስን ለማሳደግ፤ ለልዩ ልዩ ማህበራዊና የጤና ችግሮች እንዳይጋለጡ ለማድረግ በማሰብ ሲሆን በቀጣይም ልዩ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ውጤታማ መሆን እንዲችሉ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .