በአገልግሎት ሰጭና አገልግሎት ተቀባይ መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር ስልጠና ተሰጠ

  • -

በአገልግሎት ሰጭና አገልግሎት ተቀባይ መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር ስልጠና ተሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደ/ማ/ዩ፡- በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በአገልግሎት አሰጣጥ ከተማሪዎች ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ላላቸው ለ60 የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የጓደኛዊ አቀራረብ/ Youth Friendly Service/ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የስርዓተ ፆታ፤ ኤች አይቪ/ኤድስና አካል ጉዳተኞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የውልሰው መላክ ከተለያዩ አካባቢዎች በመምጣት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ወጣቶች በመሆናቸው ያልተፈለጉ ባህሪያት በማሳየት ለልዩ ልዩ ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡ ግልጋሎት ከሚሰጡ የስራ ክፍሎች (ቤተ-መፅሐፍት፣ ምግብ ቤት፣ የመኝታ ቤት ፕሮክተሮች እና የጥበቃ ሰራተኞች)  ጋር በመግባባት ተገቢውን ግልጋሎት ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ በማሰብ እና በአገልግሎት ሰጭና ተቀባይ መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ ስልጠናው እንደተዘጋጀ ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ የውልሰው አያይዘውም ይህን ስልጠና የተከታተሉ ሰልጣኞች ወጣቶች የሚያሳዩአቸውን ባህሪያት በመረዳትና እንደየባህሪያቸው በመቅረብ ቤተሰብ ለልጆቹ  የሚያደርገውን እንክብካቤ በማድረግ ለልዩ ልዩ ችግሮች እንዳይጋለጡ ተገቢውን የመከላከል ስራ እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ በቀጣይም የስልጠናውን ውጤት የመገምገም፤ የመደገፍና የመከታተል ስራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት  የሚድዋይፈሪ ትምህርት ክፍል መምህርት የውብምርት ሻረው ተማሪዎች በወጣትነት ጊዜያቸው ልዩ ልዩ ያልተገቡ ባህሪያትን ስለሚያሳዩ ተገቢውን የአቻ ለአቻ ግልጋሎት ማግኘት እንዲችሉ ያለመ ስልጠና እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ እንዲሁም የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ስሜታዊነት ስለሚያመዝንባቸው ከነዚህ ችግሮች መውጣት እንዲችሉ የወጣትነት ባህሪያት፣ ስነ-ተዋልዶና ጤና እንዲሁም ኤች አይቪ/ ኤድስና መከላከያዎች የሚሉት ጉዳዮች በስልጠናው የተካተቱ  መሆኑን አብራርተዋል፡፡ መምህርት የውብምርት ስልጠናውን የተከታተሉ ሰልጣኞች ከወጣቶች ጋር ሊኖር የሚገባቸውን ግንኙነት ለማስገንዘብ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ስልጠናውን የተከታተሉ ሰልጣኞች በበኩላቸው ያልተፈለጉ ባህሪያትን የሚያሳዩ ተማሪዎችን እንዴት መቅረብና ማስተካከል እንደሚቻል ግንዛቤ ያገኙ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ለወጣቶች ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ከልዩ ልዩ ችግሮች መከላከል እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .