በሙስና መከላከልና በስነ-ምግባር ዙሪያ ለ2ዐዐ9 ዓ.ም. ተመራቂዎች ስልጠና ተሰጠ

  • -

በሙስና መከላከልና በስነ-ምግባር ዙሪያ ለ2ዐዐ9 ዓ.ም. ተመራቂዎች ስልጠና ተሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት የ2ዐዐ9 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎች በሙስና መከላከልና በስነ-ምግባር የተሻለ ግንዛቤ ይዘው እንዲወጡ በ2 የዩኒቨርሲቲው መምህራን አስፈላጊ በሆኑ ይዘቶች ላይ ከ24-3ዐ/ዐ8/2ዐዐ9 ዓ.ም. በአዲሱ አዳራሽ ስልጠና ተሠጠ፡፡

 የስልጠናውን መድረክ የከፈቱት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰብስቤ ሞገስ እንደገለጹት የ2ዐዐ9 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎች እንደመሆናቸው ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በስራም ሆነ በማህበራዊ ጉዳዩች በሚደረጉበት ጊዜ በሙስና መከላከልና በስነ-ምግባር ላይ እራሣቸውን ብቁ አድርገው ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉ ስልጠናው አስፈላጊ በመሆኑ በአግባቡ መከታተል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርትና ስነ-ባህሪ ተቋም መምህር የሆኑት አቶ አስቻለ ታደገ እና የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ዜጋ መምህር የሆኑት አቶ ምስጋናው አዲስ ሰልጣኞች የ2ዐዐ9 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎች እንደመሆናቸው መጠን የተለያዩ ነገሮች ሊገጥሟቸው ስለሚችሉ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በሙስና መከላከልና በስነ-ምግባር ላይ በሚሰጠው ስልጠና በአግባቡ መከታተል እንዳለባቸው በበኩላቸው ገልፀዋል፡፡

ሙስና ማለት ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ከመስራት ይልቅ ስልጣንና ኃላፊነትን መከታ በማድረግ ህግና ሥርዓትን በመጣስ የመንግስትንና የህዝብ ሀብትና ንብረትን መስረቅ፣ መዝረፍ፣ ማጭበርበር እንዲሁም በጉቦ፣ በዝምድና፣ በትውውቅ በጐሰኝነት፣ በፖለቲካ ወገንተኝነትና በሐይማኖት ትሥሥር በመመርኮዝ ፍትህን እያዛቡ የግል ጥቅምን ማካበትና ሌላውን ወገን ተገቢ ባልሆነ መንገድ መጥቀም ወይም መጉዳት እንደሆነ አሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡

የሙስና ወንጀል ልዩ ባህሪያት የሚባሉት የአፈፃፀሙ ሂደትና ስልት ስውርና ውስብስብ ብዙ ሰዎችን ያሳተፈ መሆኑ፣ በአብዛኛው ማህበረሰብ ዘንድ ለጉዳዩ ባለቤት ነኝ ባይ አለመኖርና እንደነውር አለመታየቱ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ሙስና የሚገለጽባቸው መንገዶችም ጉቦ፣ ህጋዊ አሰራርን ለማስቀየር የሚሰጥ ማንኛውም መደለያ፣ ከተገልጋይ የሚሻና ከአገልጋይ የሚጠየቅ ምዝበራ፣ ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጠን ስልጣንና ኃላፊነት በመጠቀም የመንግስትን ሀብትና ንብረት መዝረፍ፣ መስረቅ፣ መውሰድና ማስወገድ፣ ማጭበርበር፣ ህጋዊ ሠነዶችን መቀየርና ሐሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት፣ የተሳሳተ መረጃ መስጠት፣ አድሎ ፣ በዝምድና፣ በዘር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በወዳጅነት ላይ ተመርኩዞ የሚሰራ ስራ እንደሆነም ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም በግንባታ ጊዜ ሊፈጸሙ የሚችሉ የሙስና ወንጀሎች፤ ክፍያ ማዘግየት፣ የፕሮጀክት ሰነዶችን መደበቅ /ማጥፋት/፣ መሰረዝ፣ የተሳሳቱ ሰነዶችን ማቅረብ የመሣሠሉት ሲሆኑ በትምህርት ተቋማት የሚታዩ የስነ-ምግባር ችግሮች ደግሞ በመምህራንና በተማሪዎች ትምህርት በወቅቱ አለመጀመር፣ የፈተና ውጤት አለማሳወቅ ስድብ፣ ፆታዊ ትንኮሳ፣ ሞራልን የሚነኩ ቃላት መናገር እና ከስርአተ ትምህርቱ ውጭ የሆነ አወዛጋቢ ጉዳይ ማንሣት ሲሆኑ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ የሰራተኛ ቅጥርን በዝምድናና በትውውቅ መስራት፣ ባልሰለጠኑበት የስራ ዘርፍ መመደብ፤ ህግና ደንብን ያለተከተለ ቅጥር መፈፀም እና የቅጥር ማስታወቂያ ሳያወጡ ወይም በተደበቀ ቦታ ላይ መለጠፍ የመሣሰሉት የሙስና መገለጫወች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የሙስና ዓይነቶች፤ ዝቅተኛ ሙስና ከመንግስትና ከህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች፣ ባለስልጣኖችና በአገልግሎት ፈላጊ ግለሰቦች የሚፈጸም ሲሆን ከፍተኛ ሙስና ደግሞ መጠነ ሰፊ የሆነ የመንግስት ሀብትና ንብረት፣ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችና በከፍተኛ የፖለቲካ አመራር አካላት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚዘረፉበትና የሚመዘብሩበት የሙስና አይነቶች ናቸው፡፡ ምሣሌ የፕሮጀክት ውሎች፣ ባንኮች፣ የገቢ ሰብሳቢዎች፣ መሰረተ ልማት ላይ የተሰማሩ መ/ቤቶች፣ ት/ቤት፣ መንገድ፣ ውሃ፣ ቴሌ፣ መብራት እና ጤና የመሳሰሉት ሲሆኑ ፖለቲካዊ ሙስና ደግሞ የአንድን ማህበረሰብ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ዕሴቶችና ልማዶችን በመጣስ የሚፈጸም ነው፡፡

የሙስና መንስኤዎች፤ የሥነ-ምግባር መበላሸት፣ የመሰረቅና የሥግብግብነት ባህሪ መኖሩና ሣይሰሩ በአቋራጭ የመክበርና የተደላደለ ህይወት መኖር፣ ለተለያዩ ሱሶች መጋለጥ፣ ከህግ በላይ የመሆን ሥሜት… የመሣሰሉት ሲሆኑ ሙስና የሚያስከትላቸው ጉዳቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ብክለት ሲሆኑ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂዎችና ስልቶች አስተዳደራዊ አሰራርና ቁጥጥርን መሰረት ያደረገ ብሄራዊ የትስስር ስርዓት መፍጠር፣ ህግን ማስፈጸም፣ ግንዛቤን ማሳደግ እና የአሠራር ሥርዓትን በማጥናት ሙስናንና ብልሹ አሰራርን መከላከል የሚቻል እንደሆነ በሰፊው ተብራርቷል፡፡

[/responsivevoice]

Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .