ከእንሰት ምርት የተዘጋጀው ምግብ እንዳስደሰታቸው በወንቃ ቀበሌ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተናገሩ

  • -

ከእንሰት ምርት የተዘጋጀው ምግብ እንዳስደሰታቸው በወንቃ ቀበሌ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተናገሩ

Print Friendly, PDF & Email

 

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር በአማራ ክልል እንሰትን ለምግብነት የማላመድ ፕሮጀክት በምስራቅ ጎጃም ዞን በአራት ወረዳዎች እየተተገበረ ይገኛል ፡፡

በወንቃ ቀበሌም ከእንሰት የተዘጋጁ ቂጣ፣ ኩኪስ ፤ ዳቦቆሎ፣ ቡላና የመሳሰሉት ምርቶች የቀመሳና ምልከታ መረሐ ግብር የቀበሌው አርሶ አደሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣ ከልማት ባንክ የመጡ ባለሙያዎች እና በእንሰት የምግብ ዝግጅት ላይ የተሳተፉ የቀበሌው ወጣቶች በተገኙበት ተካሄዷል፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is enset2.jpg

በመረሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ.ር ታፈረ መላኩ እንደገለጹት እንሰትን ለምግብነት መጠቀም የተጀመረው በጥንት አባቶቻችን እንደሆነ መረጃዎች ቢያሳዩም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን እንሰትን ማህበረሰቡ ለምግብነት ሳይጠቀምበት ቆይቷል፡፡ ማህበረሰባችን ሰፋፊ የእርሻ መሬት ባለቤት ቢሆንም የተመጣጠነ ምግብ ባለመጠቀሙ ለረሃብና ለመቀንጨር ተጋልጧል፡፡ በመሆኑም በአካባቢው በጓሮው እንሰትን በመትከል ለምግብነት መጠቀም ይኖርበታል፡፡ በሌላ በኩል ከእንሰት የሚገኘውን ምርት ከራስ ፍጆታ አልፎ ወደ ገበያ በማውጣት ተጨማሪ ሀብት ማፍራትም ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል ፡፡ በየአካባቢው ከተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው ለተቀመጡ ስራ ፈላጊ ወጣቶች በእንሰት ስራ ላይ ቢሰማሩ ተጨማሪ ሀብት ማፍራት እንደሚቻል ይህ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is enset3.jpg

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ሀይማኖት ረታ እንደገለጹት እንሰትን ለምግብነት ለመጠቀም በአማራ ክልል በ8 ወረዳዎች በ32 ቀበሌዎች ለመስራት ዕቅድ ቢያዝም አሁን ላይ በ3 ወረዳዎች ብቻ እየተተገበረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ እንሰት ለቂጣ ፣ለገንፎ፣ ለኩኪስ ፣ ለዳቦ ቆሎ፣ ለአጥሚት፣ ለቃጫ፣ ለአረቄ፣ ለአፈር ማዳበሪያነት እንዲሁም ለእንስሳት መኖነት እንደሚያገልግል የገለፁት ዶ.ር ሃይማኖት እስካሁን ማህበረሰቡ ሳይጠቀምበት መቆየቱንም ተቅሰዉ ከዚህ በኋላ እንሰትን በጓሮው በመትከል የተመጣጠነ ምግበ መመገብና ወደ ገበያ በማውጣት ተጨማሪ ሀብት ማግኘት እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡

የእንሰት ምርትን ለማስፋፍት ከ70 ሺ በለይ የእንሰት ችግኝ በማዘጋጀት ለአካባቢው አርሶ አደሮች ለማከፋፈል በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልፀው በዚህ ላይ ወጣቶች በንቃት በመሳተፍ የራሳቸውን ሀብት እንዲፈጥሩ ለሌሎች የአካባቢው አርሶ አደሮችም የእንሰት አምባሳደር በመሆን እንዲያስተምሩ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በጎዛምን ወረዳ በተመረጡ ት/ቤቶች እና በገዳም ለሚኖሩ መነኮሳት እንሰትን እንዴት ለምግብነት እንደሚዘጋጅ ለማስተማር ዕቅድ መያዙንም ገልፀዋል፡፡

በእንሰት የምግብ ቀመሳ መረሐ ግብር ላይ ተገኝተው ሀሳባቸውን የሰጡት አርሶ አደሮችም እንደገለጹት እስከ አሁን የእንሰት ምርትን በጓሯችን በአካባቢያችን ቢኖርም ለእንስሳት መኖነት ሲጠቀሙበት እንደቆዩና አሁን ግን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ልማት ጋር በመተባበር ለምግብነት ለማዋል ባደረገው የእንሰት ምገባ ቀመሳ መረሐ ግብር ላይ ተገኝተን ቀመሳ በማካሄዳችንና በመሳተፋችን ተደስተናል፤ የቀመስነው የእንሰት ምግብም ጣፋጭነቱ በጣም ጥሩ ነው፤ እስካሁንም እንሰት ለምግብነት መዋሉን ባለመረዳታችንና ባለመጠቀማችን ተፀጽተናል ሲሉ ሀሳባቸውን በቁጭት ገልፀዋል፡፡

የእንሰትን ተከል በሰፊው በጓሮ በመትከል ለምግብነት ለመጠቀም ዝግጁ እንደሆኑና ወደ ገበያ በማውጣት ተጨማሪ ሀብት ለማግኘት ዕቅድ እንዳላቸው፤ ይህንንም ለማሳካት ዩኒቨርሲቲው የእንሰት መስሪያ ቁሳቂሶችን ድጋፍ ቢያደርግልን ከእኛ አልፎ ለክልላችን ብሎም ለሀገራችን የእንሰትን ምርት ወደ ገበያ ለማቅረብ ፍላጎት አለን ሲሉም ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡

 


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .