ወጣቶችን በስፖርታዊ ስነ-ምግባር በመገንባት ከሱስ ነጻ ትውልድ ለመፍጠር እየሰራ እንደሆን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

  • -

ወጣቶችን በስፖርታዊ ስነ-ምግባር በመገንባት ከሱስ ነጻ ትውልድ ለመፍጠር እየሰራ እንደሆን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደማዩ ታህሳስ 2013ዓ/ም፡- የዩኒቨርሲቲው ማህ/አገ/ዳይሬክቶሬት ከምስ/ጎጃም ዞን የወርልድ ቴኮንዶ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር  የምስራቅ ጎጃም ዞን ከሁሉም ወረዳዎች  የተመረጡ ወጣቶች የተሳተፉበት የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር  ከታሃሳስ 9-11/2013ዓ/ም በቢቸና  ከተማ ተካሄደ፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን  የወርልድ ቴኮንድ  ፌደሬሽን  ፕሬዚዳንት ኢንስፔክተር አልማው ወርቅየ  የውድድሩን ዋና አላማ አስመልክተው እንደገለጹት  ስፖርቱ ከኮረና ቫይረስ በሽታ መከሰት ጋር ተያይዞ የመቀዛቀዝ ሁኔታ የታየበት ሲሆን ወጣቱም አልባሌ ቦታ በመዞር  እና በሱስ ተጠቂ እየሆኑ በመምጣታቸው ይህን የስፖርት  ውድድር እንደ ማነቃቂያ  በማዘጋጀት ወጣቱ ከነበረበት ሱስ እንዲነጻ የስፖርት ውድድሩን ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢንስፔክተር  አልማው ወርቅየ አክለው እንደተናገሩት  ቴኳንዶ   የሚሰለጥኑ  ወጣቶች  በአምሯዊና ስነልቦናዊ አቋማቸው  ጠንካራ የሆኑ፣ ከተለያዩ ሱሶች የጸዱና ለሌሎች ወጣቶችም ዓርዓያ በመሆናቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመጠናከር እንደ ሃገር   ያለብንን  ክፍትት  ለመሙላት  ሰፊ እድል እንደሚፈጥር  ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምር/ማህ/አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ምህርት አለማየሁ ውድድሩን አስመልክተው እንደተናገሩት  ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ  ወጣቱን በስፖርት ዘርፍ ለማሰልጠን የተለያዩ ሙያዊ ድጋፎችን ሲያከናውንና እንደ ምስራቅ ጎጃም ዞንም የነበረውን የዳኛ ችግር ለመቅረፍ ለ10  ዳኞች ስልጠና መሰጠቱን  አውስተው  ይህ  ውድድርም  የዚህ አንዱ አካል በመሆኑ  ዞኑ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ለውድውሩ  ግብዓት  የሚሆኑ ወጭዎችን ዩኒቨርሲቲው ሽፋን እንዳደረገ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ምህረት አክለውም ወጣቱ  የቴኳንዶ ስፖረቱን ባህል በማድረግ  ከአልባሌ ቦታ እንዲመለስ ፣ስራ እንዲፈጥር ፣በስነ-ምግባሩ የተሻለና አርዕያ  በመሆን በሃገር ደረጃ ተወዳዳሪና አሸናፊ   እንዲሆኑ   የቁሳቁስ ፣የአሰልጣኝ  ዳኛዎች፣የቴኳንዶ አሰልጣኞችና ለወጣቶች  ዩኒቨርሲቲው  በማማከር፣ በስልጠናና እና በቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትም/ክፍል መምህርና በውድድሩ ዳኛ የነበሩት  መምህር ሞላልኝ እንቻለው እንደገለጹት ቴኳንዶ የእጅና የእግር ጥበብን የሚጠቀም አንዱ የስፖርት ጥበብ እንደሆነ ገልጸው ስፖርቱ በብዛት የሚዘወተረው ደቡብ ኮሪያ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርትም  በኢትዮጵያ እየተለመደ  መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

እንደ ትምህርት ክፍል  የማማከርና ስልጠናዎችን የመስጠት ፣ወጣቱ ወደዚህ  ስፖርት  እንዲገባ  ግንዛቤ የመፈጠር  ስራዎችን እንደሚሰሩ የተናገሩት መምህር ሞላልኝ ፤ዩኒቨርሲቲው  እንዲህ ያሉ ስፖርቶችን  ለመደገፍ በአካባቢው ያሉትን  የቴኳንዶ አሰልጣኞችን የማበረታታትና የመደገፍ ስራ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

በውድድሩ እንደየተሳተፉበት ክብደታቸው  አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች  የሜዳልያና ዋንጫ  ሽልማት  ከምስራቅ ጎጃም ዞን የወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን  ተበርክቶላቸዋል፡፡

 


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .