የሴቶች የአመራር ብቃት ስልጠና ተሰጠ

  • -

የሴቶች የአመራር ብቃት ስልጠና ተሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ሴት መምህራንና ሠራተኞች በአመራር ብቃት ላይ የሁለት ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናውን ያዘጋጀው በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ሲሆን ዓላማው ሴቶችን ወደ አመራርነት ማምጣት የሚቻልበትን ብቃት ማስታጠቅ እንደሆነ ተገልጿል፡፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይና ኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የውልሰው መላክ በከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ አመራር ቦታዎች ላይ የተቀመጡ ሴቶች ቁጥራቸው በጣም አነስተኛ ስለሆነ ይህንን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ሴቶች በየተመደቡበት ቦታ ሁሉ አመርቂ ሥራ በመስራት የአመራር ብቃታቸው ማሳደግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ወ/ሮ ጥሩዓለም አወቀ የሴቶች ወደ አመራርነት መምጣት ለተቋሙ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ስለሆነ ሁልጊዜ የአመራር ጥበብ ሥልጠናን በንቃት በመሳተፍ የአመራርነት ሚና ሊጫወቱ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የአመራር ምንነትና የጥሩ አመራር ሥነ-ምግባር፣ የአመራር ችሎታና ብቃት እንዲሁም የሴቶች አመራር በሚሉ አርዕስቶች ዙሪያ ገለፃዎችና ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ በውይይቱ ወቅትም የሴት አመራር አስፈላጊነትና ሴቶች አመራር እንዳይሆኑ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች በሠፊው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊ ሴት መምህራንና ሰራተኞች ስልጠናው በጣም ጥሩ እንደነበር በመግለፅ ቀጣይነት እንዲኖረው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .