የሸበል በረንታ የተቀናጀ የአቅም ማጎልበቻ ልማት ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ዓውደ ጥናት ተካሄደ

  • -

የሸበል በረንታ የተቀናጀ የአቅም ማጎልበቻ ልማት ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ዓውደ ጥናት ተካሄደ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እና አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ በትብብር የሚያከናዉኑት የሸበል በረንታ የተቀናጀ የአቅም ማጎልበትና የልማት ፕሮጀክት የሚል የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ፤ የዞኑንና የወረዳዉ ከፍተኛ አመራሮች፤ የክልሉ የገንዘብ ቢሮ እና በየደረጃዉ ያሉ የማህበረሰቡ ተወካዮች በተገኙበት ሸበል በረንታ ወረዳ የዕድዉሃ ከተማ ተካሄደ፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%88%B8%E1%89%A0%E1%88%8D2.jpg

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት  አቶ ዉብሸት ዳምጤ የሸበል በረንታ ዋና አስተዳዳሪ ሲሆኑ በንግገራቸዉም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በወረዳችን ላይ  ያለዉን የመገዳደል (የደም መመላለስ) ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ለማስወገድ በማሰብ የእርቅ ማድ ፕሮግራም እንዲተገበር በማድረግ ወደ አርባ ያህል ግጭቶችን  በአንድ አመት ወስጥ እንዲፈቱ  አስተዋጾ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ አሁን ደግሞ ከአግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ፕሮጀክት በመቅረጽ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል ፡፡

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ሸበል በረንታ ወረዳ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ለአካባቢዉ ማህበረሰብ አለኝታ ሆኗል፡፡ በተለይ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ላይ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በሰብል ልማት ስራ ላይ ዘለቄታዊነት እንዲኖረዉ በማሰብ ፍኖተ በላይ የራስ አገዝ የህብረት ስራ ማህበርን አቋቁሞ ወደ ስራ ግብቷል፡፡ የህብረተሰቡን አንኳር የሆነውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ፕሮጀክት በመቅረፅ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ 

ከወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ በርካታ ስራዎችን ለአብነትም ፦ እንስሳት ማድለብ፣ ደሮ እርባታ፣ ፍየል እርባታ ናቸዉ፡፡ ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችን በመታገል እና በወረዳዉ እንዲቀንስ በማድረግ የራሱን ሚና ተወጥቷል፡፡ አሁን ደግሞ በአዲስ ራዕይና መንፈስ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ይህንን ፕሮጀክት ቀርፀዉ  ወደ ስራ ለመግባት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ነዉ በማለት  ፕሮግራሙን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%88%B8%E1%89%A0%E1%88%8D3.jpg

አቶ ተመስገን ወንድይፍራዉ የአግሪ አርቪስ ኢትዮጵያ የሸበልና የሁለት እጁ ፕሮጀክት ማናጀር  የሸበል የተቀናጀ የአቅም ማጎልበት የልማት ፕሮጀክት  ላይ አጭር ገለጻ  ያደረጉ ሲሆን በገለጻቸዉም  ፕሮጀክቱ ዓለማ ምን ይመስላል፣ ፕሮጀክቱ ያጋጠሙት ችግሮች፣ አፈጻፀም እና የአተገባበር ስልቶች፣ተጠቃሚዎች እነማን ናቸዉ፣ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ስለአደረጉት ስምምነት፣ ከወረዳዉና ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል?  የሚሉ ነጥቦችን ትኩረት አድርገዉ አጠር ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ወደ ጎጃም አካባቢ ከመጣ ወደ 30 አመት አካባቢ እንደሆነውና ወደ ሸበል በረንታ ወረዳ ከገባ ደግሞ 6  አመት እንደሆነዉ በመግለፅ አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ  በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚያከናዉናቸዉ ተግባራት በምግብ ዋስትና፣ አየር ንብረትና ተፈጥሮ ሃብት ልማት፣ የስራ ዕድል ፈጠራ እና የገቢያ ትስስር፤ አቅም ማጎልበትና የህብረት ስራ ልማት ማህበራትን ማቋቋም ላይ እንደሆነ ገልፀዋል።

ይህ ፕሮጀክት የ 3 አመት ፕሮጀክት ሲሆን  በዘጠኝ ቀበሌዎች እንደሚተገበርም አንስተው  5700  የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ እና 31.8 ሚሊዮን ብር ወጭ እንደሚጠይቅም አብራርተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማዎችም 350 ሄክታር የተራረቆጠ አካባቢን መልሶ እንዲያገግም ማድረግ፤ ፍኖተ በላይ የራስ አገዝ የልማት ማህበርን ራስ ማስቻል፤ የልማት ተሳትፎን በዘላቂነት ማረጋገጥ ለአሁኑና ለመጭዉ ትውልዶች ምቹ አካባቢን መፍጠር መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀረበው ፕሮጀክት እና አተገባበሩ ዙሪያ ወይይት የተደረገ ሲሆን  በዉይይቱም  የተነሱ ነጥቦች መካከል ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እና አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ በሸበል በረንታ ወረዳ እየሰሩ ያሉት ስራ የሚበረታታ እንደሆነ ተገልጿል።

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%88%B8%E1%89%A0%E1%88%8D4.jpg

ዶ/ር አስካለማሪያም አዳሙ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት በበኩላቸው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ላይ ትኩረት ሰጦ እየሰራ መሆኑን ገልጸው  ለዚህም ብቁ አመራር እየሰጡ ያሉትን  የዩኒቨርስቲያችንን ፕሬዘዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩን አመስግነዋል፡፡ ለወደፊትም ከመማር ማስተማር እና ችግር ፈች ጥናትና ምርምሮች ከማድረግ ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎትን አጠናክሮ  እንደሚቀጥል  አርጋግጠዋል፡፡

አቶ አበበ መኮንን የም/ስ/ጎ/ዞን ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊ እንደተናገሩት ደግሞ ም/ስ/ጎ/ዞን እንደ ሀገር ትርፍማ አምራች አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው እንደ ትርፍ አምራችነቱ ግን እየተጠቀመ እንዳልሆነ ተናግረዋል። የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች (Overlap) እንዲያደረጉ ክትትል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

 

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%88%B8%E1%89%A0%E1%88%8D5-1.jpg

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ በዉይይቱ ማጠቃለያና መዝጊያ ንግራራቸዉ እንደተናገሩት  ከተረጅነት በመወጣት እራሳችንን መቻል እንደሚገባ፣   የወረዳዉ ማህበረሰብ ጠንክሮ በመስራት እራሱን መለወጥ እንደሚገባው፤ በፕሮጀክቱ የሚታቀፉ ሰዎችን በአግባቡ መምረጥ እንደሚገባና ፕሮጀክቱ ሁለገብ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

የሚሰሩ ፕሮጀክቶችም ጥራታቸዉን የጠበቁ እንዲሆኑ የፕሮጀክት ትግበራ ዲስፒሊን በመከተል ሂደቱን በየጊዜዉ መገምገም እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም የዕድ ዉሃ ከተማ ላይ አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ያለማውን የቦረቦር መሬት ጉብኝት ተደርጎ መርሃ ግበሩ ተፈፅሟል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .