የተፈጸመዉን ነፍስ ማጥፋት የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲን እና የከተማዋን ገጽታ ለማበላሸት መሆኑ ተገለጸ

  • -

የተፈጸመዉን ነፍስ ማጥፋት የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲን እና የከተማዋን ገጽታ ለማበላሸት መሆኑ ተገለጸ

Print Friendly, PDF & Email

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የተፈጠረዉን ግጭትና ህይወት መጥፋት ምክንያት በማድረግ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች  ጋር ወይይት አካሄዱ፡፡

ወይይቱ የተጀመረዉ በግጭቱ ህይወቱን ያጣዉ ተማሪ  ለማሰብ  የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ነው፡፡ የደብረማርቆስ ዪኒቨርስቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ወንጀሉ የዩኒቨርስቲዉን ገጽታ ለማበላሸት ሆን ተብሎ የተፈጸመ በመሆኑ ድርጊቱን እንደሚያወግዙት በመግለጽ የወንጀሉን ፈጻሚዎች ለህግ ለማቅረብ በሚደረገዉ ሂደት ለህግ አካላት አስፈላጊዉን ትብብር እንደሚያደረጉ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረዉ ግጭትና ነፍስ መጥፋት  የደብረማርቆስ ዪኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች፣የምስ/ገጃም ዞን ከፍተኛ አመራሮች ከደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪዎችና ሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ወይይቱ የተጀመረዉ በግጭቱ ህይወቱን ላጣዉ ተማሪ  ለአንድ ደቂቃ የህሊና ጾሎት በማድረግ ሲሆን በተፈጸመዉ ነፍስ ማጥፋት የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸዉና የከተማዋን ገጽታ ጥላሸት ለመቀባት ሆነ ተብሎ የተቀነባበረ ስለሆነ እንደማይቀበሉት እና ፈጽሞ እንደሚያወገዙት እንዲሁም የወንጀሉን ፈጻሚዎች ለመያዝ በሚደረገዉ ሂደት  ለህግ አካላት  አስፈላጊዉን  ትብብር እንደሚያደረጉ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም፡- ህይወቱን ላጣዉ ተማሪ ነፍሱን በአጸደ ገነት ፈጣሪ እንዲያኖራትና ለቤተሰቦቹ ጓደኞቹ እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መጽናናትን ሁሉም የውይይቱ ተሳታፊዎች ተመኝተዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .