የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥና ለማዝለቅ የሚፈጸሙ ተግባራት ላይ ውይይት አደረጉ፡፡

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥና ለማዝለቅ የሚፈጸሙ ተግባራት ላይ ውይይት አደረጉ፡፡

Print Friendly, PDF & Email

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ሰላማዊ ለማድረግና ለማዝለቅ ከሳይንስና ትምህርት ሚኒስቴር በወረደው አጀንዳ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳት አቶ ታደሰ ጤናውና የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን ጋር በሰላማዊ መማር ማስተማር ዙሪያ ውይይት ሲያድርጉ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት  በእውቀቱ  በክህሎቱ፣ በአመለካከቱ ብቁ ሁኖ ስራ ፈጣሪ፣ አገር ወዳድ  እና ሃላፊነታቸውን  በአግባቡ የሚወጡ ምሩቃንን  ለማፍራት ለተሰጧቸው ተልኮዎች  በርካታ ተግባራትን  እንደሚያከናውኑ ይታወቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ከአራቱ ማዕዘናት  የሚቀበሏቸውን  ተማሪዎች  ሁለንተናዊ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በየሰለጠኑባቸው የትምህርት ዘርፎች ተመርቀው  ወደ እየመጡበት እንዲመለሱ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

በአለፉት ሁለትና ሶስት አመታት  በአለው አገራዊ ሁኔታ  ምክንያት  ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት  ለችግር ተጋልጠው ቆይተዋል ያሉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉደዮች ምክትልፕሬዜዳንት አቶ ታደሰ ጤናው  ይህንን ለመቅረፍና ለመከላከል የሳይንስና ከፍተኛ  ትምህርት ሚኒስቴር  በ2012 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች  ሰላማዊ መማር ማስተማር  ሂደትን  ለማረጋገጥና ለማዝለቅ  ባዘጋጀው ሰነድ ላይ  ባለድርሻ አካላት ውይይት  በማድረግ  የሚጠበቅባቸውን ሚናና ሃላፊነት  እንዲወጡ  ለማድረግ  የተዘጋጀ ውይይት  እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አቶ ታደሰ  ባቀረቡት የሳይንሳና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሰላማዊ መማር ማስተማር  ሂደትን  ለማረጋገጥ  እና ለማዝለቅ  በሚለው ሰነድ ላይ  እንደጠቆሙት  በ2011 ዓ.ም  የትምህርት  ዘመን  በሰላማዊ መማር ማስተማር  የነበሩ ዋና ዋና ችግሮች፣  የመልካም  አስተዳደር፣ በቂና ብቁ  የሰው ሀይል  አለመሟላት፣ የዩኒቨርሲቲው  አመራር፣ መምህራንና ሰራተኞች ሃላፊነትና ተጠያቂነት  በየደረጃው አለመኖሩ  እንዲሁም  የነባር  አደረጃጀቶች  መዳከምና አልፎ አልፎ  መጥፋት ነው ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች የተከሰቱ ችግሮችም የዩኒቨርሲቲዎች ሰላም እንዲደፈርስ፣ የንብረት ውድመት እንዲከሰት፣የአካልናየህይወት  መጥፋት እንዲኖርና ህብረተሰቡ በዩኒቨርሲቲዎች አመኔታ  እንዳይኖራቸው ያደረገ መሆኑን አቶ ታደሰ አክለው ገልጸዋል፡፡

የችግሮችና የተግዳሮቶች መነሻም ስራዎችን ለመከታተል ፈጣንና የተጠናከረ  የተቀናጀ  የመረጃ ስነ ስርዓት  አለመዘጋጀት፣  ወጥነት ያለው የእቅድና ሪፖርት  ዝግጅት  ክትትል እንዲሁም  የግብረ መልስ  ስርዓት አለመኖሩ፣  በተለያየ ምክንያት ሰራተኛው  ሲሰራበት  የነበረውን ቦታ  ሲለቅ  የስራ እርክክብ አለማድረግ እንደሆኑ  ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሰላማዊ የመማር ማስተማር  ሁኔታ  ለመፍጠር ሁሉም  ባለድረሻ አካላት  የግጭት  መንስኤ  ከመሆን  ይልቅ  ችግር እንዳይፈጥሩ  አበክሮ መስራት፣ የሚያጋጥሙ  ችግሮችን  ወዲያውኑ  መፍታትና  የችግሩ  የመፍትሄ  አካል መሆን  እንደሚገባም አቶ ታደሰ  አሳስበዋል፡፡

ለዚህም  የተማሪዎችን መሰረታዊ አገልግሎቶች በአግባቡና በበቂ ሁኔታ እንዲሟሉ ማድረግና ምቹ የመማር መስተማር ሁኔታ እንዲኖር ለማድረግ  ስምምነት ላይ  ተደረሷል፡፡

በተያያዘ ዜና የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ መምህራንና ሰራተኞች  ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህረት ሚኒስቴር በተዘጋጀው ሰላማዊ መማር ማስተማር  ሄደትን  የማረጋገጥና  የማዝለቅ ሰነድ ላይ ውይይት አድረገዋል፡፡

በውይይቱም የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን በሰላማዊ ሁኔታ  ካምፓሱ  ማጠናቀቁን አስታውሰው የ2012 ዓ.ም  የትምህርት አመትንም ሰላማዊ ለማድረግና ለማዝለቅ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ  ጠንክሮ  ሊሰራ እንደሚገባው ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .