የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ኦስትሪያ ሀገር ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የጂ አይ ኤስ ስልጠና ሠጠ

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ኦስትሪያ ሀገር ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የጂ አይ ኤስ ስልጠና ሠጠ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደ/ማ/ዩ፡- በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአፒር /APPEAR Project/ ለመሬት አስተዳደር ተቋም ባለሙያዎችና ከGIS ጋር ተያያዥነት ያለው ስራ ለሚሰሩ ሌሎች ባለሙያዎች የGIS ስልጠና ሠጠ፡፡

ስልጠናውን የሠጡት ተመራማሪ አቶ ማርቪን ኩትቻን ስልጠናው መሠረታዊ የGIS አጠቃቀም ስልጠና እንደሆነ እና የሚያተኩረውም በመሬት አስተዳደር ዙሪያ መሆኑን በመግለጽ ዋና አላማውም ለመሬት አስተዳደር ባለሙያዎች የGIS ቴክኖሎጂን ማሳወቅ እና እውቀትን ማሸጋገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ  የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዚዳንትና የAPPEAR ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ሳይህ ካሳው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከኦስትሪያ ሀገር ከሚገኙ TUW እና BOKU ዩኒቨርሲቲዎችና እንዲሁም ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመሬት አስተዳደር ተቋም ጋር ትብብር እንደመሠረቱ በመግለጽ በምርምር፣ በመማር ማስተማር እና በማህበረሠብ አገልግሎት ዙሪያ ሊተገበር የሚችል ፕሮጀክት በማዘጋጀት ለ4 ዓመት ያህል የሚቆይ ፈንድ ማግኘት እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡

የዚህ ፕሮጀክት ዓላማ በዋናነት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመሬት አስተዳደር ተቋም መክፈትና ያለውን የሠለጠነ የሠው ሀብት እጥረት መቅረፍ ነው በዚህም የአቅም ግንባታ ስራ እንደተካተተ እና በዘርፉ የዳበረ ልምድ ያላቸው ተመራማሪዎች ከኦስትሪያ በመምጣት አጫጭር ስልጠናዎችን እየሠጡ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ሳይህ ካሳው አያይዘውም በዘርፉ ብዙም የሠለጠነ የሠው ሃይል የማይገኝበት በመሆኑ እና በርካታ ሀገራዊ ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው በማመን ፕሮጀክቱን መተግበር የመሬት አስተዳደር ተቋም ባለሙያዎችን አቅም ማሳደግና ቁጥራቸውን መጨመር ዋና ትኩረት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በዚህ መሠረት በGIS ዙሪያ የተሠጠው ስልጠና ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመሬት አስተዳደር ተቋም ባለሙያዎች፤ ለግብርናና ሌሎች  የትምህርት ክፍሎች ባሙያዎች እንዲሁም ከወረዳና ዞን ለተውጣጡ ከGIS ጋር በተያያዘ ስራ ለሚሠሩ ለተመረጡ ባለሙያዎች በድምሩ ለ24 ባለሙያዎች ለተከታታይ 5 ቀናት ያህል በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሠጠቱን አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም የመሬት አስተዳደር 2ኛ አመት 42 ተማዎች የሪሞት ሴንሲንግ /remote sensing/ ኮርስ በዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ባለው ፕሮፌሠር/ ተመራማሪ እንደተሠጠ ገልፀዋል፡፡

ስልጠናውን የተከታተሉ ሙያተኞች በበኩላቸው የዚህ አይነት ስልጠናዎች መሰጠታቸው ያለባቸውን የክህሎት እና እውቀት ክፍተት የሚሞላ ከመሆኑ ባሻገር ልምድም ያገኙበት እንደሆነ በመግለፅ ሌሎች ስልጠናዎችም መሰጠት ቢችሉ ጥሩ እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .