የግንባታ ሥራዎች በተፈለገው ጊዜ ተሰርተው ለተፈለገው ዓላማ እንዲውሉ ቁጥጥርና ክትትል ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

  • -

የግንባታ ሥራዎች በተፈለገው ጊዜ ተሰርተው ለተፈለገው ዓላማ እንዲውሉ ቁጥጥርና ክትትል ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባቸው ያሉ ህንፃዎችን በተመለከተ የ2010 ዓ.ም የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡ ግምገማዉ ከተቋራጭ ድርጅት ባለቤቶች፣ ከአማካሪ ድርጅቶች የበላይ ሀላፊዎች፣ የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊዎችና ከየፕሮጀክት ሳይቱ ሀላፊዎች ጋር ሲሆን በግምገማውም ከአማካሪዎች ጋር በሩብ ዓመቱ አፈፃፀም ላይ የታዩ ችግሮችን በማንሳት የመፍትሄ እርምጃ እያስቀመጡ ለቀጣይ ሩብ ዓመትም የትኩረት ነጥቦችን ለይቷል፡፡

ተቋራጮች የ2ኛው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ሁሉም ግንባታዎች ከተሰጣቸው የጊዜ ገደብ በላይ የሄዱ ቢሆንም ስራዎቻቸው ግን ያላለቁና የዘገዩ እንደሆነ ከቀረበው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከሪፖርቱ በኋላም በእያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ ያሉ ጠንካራ ጎኖችና መስተካከል ያለባቸው ነጥቦች ተነስተው ስራዎችን ወደ ሳይት በመሄድ ጉብኝት ተደርገዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት  ዶ/ር ሳይህ ካሳው በጉብኝቱ ወቅት ታምራት ተመስገን ህ/ስ/ተቋራጭ እያስገነባ ያለው የመምህራንና ሰራተኞች መዝናኛ ከሚገባው ጊዜ በላይ  እየወሰደ ያለ ፕሮጀክት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አማካሪውም ሆነ ባለቤቱ በግድየለሽነት እንደያዙት በመግለፅ ያሉትን ጥቃቅን ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ርክክብ መፈፀም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ዳንኤል ሱሊቶ የሚያስገነባው የመማሪያ ክፍል ግንባታ ከበፊቱ በተሻለ ፍጥነት እየሄደ ቢሆንም ስራውን በወቅቱ ለማጠናቀቅ እንዳልቻለ ታይቷል፡፡አሁንም የድርጊት መርሀ ግብር ተሰርቶለት በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ እንዳለበትና ጥራት ያለው አሸዋ መጠቀም እንዳለባቸው ተገልጧል፡፡

የአዳራሽ ግንባታውና የጤና ካምፓስ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮም በተመሳሳይ የማጠናቀቂያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ስራዎች ያላለቁ እንደሆኑ በመግለፅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ርክብክብ መፈፀም እንዳለባቸው ዶ/ር ሳይህ ካሳው አክለው አሳስበዋል፡፡

ከፍሊንትስቶን ኢንጅነሪንግ፣ ሳፍር ኮንሰትራክሽን እና ከስሪኤም ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ባለቤቶች ጋር ስለ ግንባታዎች ሁኔታ የሶስትዮሽ ውይይት በጥቅምት ወር እንደተደረገም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ እየተገነቡ ያሉ ግንባታዎች አፈፃፀም ሲታይ ሁሉም የዘገዩና መጠናቀቅ ባለበት ጊዜ ያልተጠናቀቁ፣ ከሚገባው ጊዜ በላይ የወሰዱና ለተፈለገው ዓላማ በተፈለገው ጊዜ ያልደረሱ እንደሆኑ በመግለፅ ቀጣይ ለአጨራረስ የሚሆኑ ቁሳቁሶችንና የሰው ሃይል ቀድሞ በማሟላት በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ርክክብ እንዲያደርጉ ተጠቁሟል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .