ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለአንደኛ አመት ተማሪዎች ኦሬንቴሽን ሰጠ

  • -

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለአንደኛ አመት ተማሪዎች ኦሬንቴሽን ሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከተሰጡት ሶስቱ ተልዕኮዎች አንዱ የመማር ማስተማር ሥራውን በስነ-ትምህርት ፋኩሊቲ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በርካታ የትምህርት ክፍሎችን በመክፈት የቅበላ አቅሙን አሳድጓል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ አመት ተማሪዎች አስተባባሪ ዶ/ር ለወየ ጌቴ  የእንኳን  ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይሄይስ አረጉ እንደተናገሩት “እናንተ በብዙ ፈተናዎች መካከል አልፋችሁ እዚህ ደረጃ የደረሳችሁ ተማሪዎች ናችሁ፡፡ ሆኖም ከትምህርቱ ባለፈ በህይወት ተፈትናችኋል፡፡ በወጣትነት ዘመን ይህን ዓይነት ችግር ማለፋችሁ የሚደነቅ ነው” ብለዋል፡፡

“የትምህርት ጊዜያችሁን በስኬት አጠናቃችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መስፈርት  አሟልታችሁ እና የነበሩ ችግሮችን አሳልፋችሁ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመድባችሁ እንኳን በሰላም መጣችሁ” በማለት ፕሬዚዳንቱ አክለው ገልጸዋል፡፡

የአካባቢው ማህበረሰብ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ አክብሮት ስላለው የዚህን ህብረተሰብ ባህል ፣ልማድ፣ መላበስ ይጠበቅባችኋል፡፡ ሆኖም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጥሩ የሆነ የመማር ማስተማር ሂደት የሚሰጥበት ስለሆነ ለአካዳሚክ ፕሮግራማችሁ ሰፊ ጊዜ በመስጠት ትምህርታችሁ ላይ ትኩረት በማድረግ ጠንክራችሁ እንድትማሩ በማለትም አሳስበዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ቢያዝን ጌትነት እንደተናገሩት “በተማሪዎች አገልግሎት ክፍል የሚሰጡት አገልግሎቶች የምግብ አገልግሎት፣ የምኝታ አገልግሎት፣ የህክምና አገልግሎት ፣ የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ፣ስፖርትና መዝናኛ፣  የዲሲፕሊንና የህግ አገልግሎት ሲሆኑ የተማሪዎች ግዴታ የሚባሉት በዩኒቨርሲቲው የተደነገገውን የመውጫ እና የመግቢየ ሰዓት ማክበር፣ ሱስ ከሚያሲዙ ነገሮች እራስን መጠበቅ ፣የወጭ መጋራት ውል መያዝ ፣ ከማንኛውም ህገ ወጥ ስራና ስነ-ምግባር ከጎደለው ተግባር መቆጠብ ፣ ማንኛውም ተማሪ ከተመደበበት መኝታ ቤት ውጭ ሌላ ዶርም ሂዶ አለመተኛት ፣ በሁለት ተማሪዎች መካከል የሚነሳ ጸብ ወደ ብሄር ተኮር ጸብ መቀየር፣ የጋራ መገልገያ ዕቃዎችን  በግል መጠቀም፣ ሆኖ ሌላው  የተማሪዎች መብት ማንኛውም በዩኒቨርሲቲው  የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማግኘት፣በቤተመጽሃፍ ውስጥ የታተሙና ያልታተሙ መጽሐፍና ኢንተርኔት መጠቀም፣ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና የዩኒቨርሲቲውን እሴቶች ማክበር፣ ዩኒቨርሲቲው የሚጠይቀውን የአገልግሎት ክፍያ መክፈል፣ ግቢውን በሚለቁበት ጊዜ  የተረከቡትን  ንብረት ማስረከብ ነው” ብለዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ  የተማሪዎች ህብረት  ምክትል ፕሬዚዳንት  ተማሪ ጌጤነህ ሸገን “እንኳን የእነ ክቡር  ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ የእነ አራት አይና ጎሹ የንጉስ ተክለ ሃይማኖት መናገሻ የድሮዋ መንቆረር የአሁኗ ደብረ ማርቆስ ከተማ እንኳን በሰላም መጣችሁ” ብለዋል፡፡

“እናንተ አዲስ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኛው  ከመምህራን ዕውቀትን፣ ጥበብን፣ ከአስተዳደር ሰራተኛው ደግሞ የአመራርነት ብቃትን  ቀስማችሁ እንደምትሄዱ  እምነቴ ነው” ሲሊ አክለው ገልጸዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .