ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

  • -

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሀምሌ 16/2014 ዓ.ም (ደ/ማ/ዩ፡- ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በመደበኛው፣በማታው እና በተከታታይ የትምህርት መርሀ ግብሮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2212 ተማሪዎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት ለ14 ኛ ጊዜ ሀምሌ 16/2014 ዓ.ም በድምቀት አስመርቋል፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is 26-1.jpg

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ተመራቂዎች አለም አቀፉን የኮሮና ወረርሽኝ እና በሀገሪቱ የነበረውን ጦርነት ተቋቁማችሁ ለዚህ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ መመደቡን ተከትሎ በግብርና፣ በሀገር በቀል ዕውቀትና በጤና ዘርፎች በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በ1999 ዓ.ም ስራውን የጀመረው ዩኒቨርሲቲው እስካሁን 54 ሺህ 874 ተማሪዎችን ማስመረቁን ገልፀው በአሁኑ ሰዓት 63 የመጀመሪያ ዲግሪ ፣ 65 ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 9 ሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is 26-2.jpg

የምረቃ ስነ-ስርዓቱ የክብር እንግዳ ፕሮፌሰር በላይ ካሳ ሲሆኑ ለተመራቂ ተማሪዎች የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is 26-3.jpg

በአሁኑ ስዓት የአማራ መልሶ ማቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ  ለተመራቂ ተማሪዎች ተጨማሪ የህይወት ክህሎት ንግግር አድርገዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is 26-4.jpg

በዕለቱ ከኮሌጆች፣ተቋማት እና ት/ቤቶች ከ1ኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ለያዙ ተመራቂዎች የምስክር ወረቀት፣ አንደኛ ደረጃ ለያዙ ተማሪዎች የሜዳሊያ እንዲሁም ከአጠቃላይ ከወንዶችና ሴቶች 1ኛ ደረጃ ለያዙ ተመራቂዎች የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል፡፡ከአጠቃላይ ወንድ ተማሪዎች 3.96 በማምጣት 1ኛ ደረጃ የያዘው ከተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ደሳለኝ ቢራራ ሲሆን ከአጠቃላይ ሴት ተመራቂዎች 3.93 በማምጣት 1ኛ የሆነችው ደግሞ ከህክምና ትምህርት ቤት እጅጋየሁ ይግዛው ናት፡፡

እነዚህ የዋንጫ ተሸላሚዎች ለዚህ ክብር በመብቃታቸው መደሰታቸውን በመግለፅ የነበረውን ወቅታዊ ችግር ተቋቁመው ለዚህ ዕድል መብቃታቸው ደግሞ ስኬታቸውን ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡

በዋናው ግቢ የተከናወነው የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኘ ሲሆን በአሚኮ ዩቱዩብ ቻናል ላይም እንደሚገኝ እየጠቆምን ሙሉ ዝግጅቱን ለመመልከት ለምትፈልጉ ከታች ሊንኩን አስቀምጠናል።

https://youtu.be/GeUYE89Sf7k


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .