ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ሃገር አቀፍ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ

  • -

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ሃገር አቀፍ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2ዐ1ዐ ዓ.ም. ብቁና ሀገር ተረካቢ ዜጋን በማፍራት ሥራው ጤታማ እንዲሆን በተለያዩ አርዕስቶች ዙሪያ በዋናው ግቢና በቡሬ ካምፓስ የተማሪዎች ግምገማዊ ስልጠና አካሄደ፡፡ የውይይቱ አላማም ዩኒቨርሲቲው ብቁና ሀገር ተረካቢ ዜጋን ለማፍራትና ውጤታማ አሰራርን ለማጎልበት ተማሪዎች እንዴት አቅደው መስራት እንዳለባቸው፣ ምን ምን ፈተናዎች እንዳሉና የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችሉ አሰራሮችን ለማስገንዘብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ስልጠናው ሴኩራሊዝምና የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ያለውን ገጽታ ግንዛቤ ለማስያዝ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለነባርና ለአዲስ መደበኛ ተማሪዎች የውጤታማነት ስኬት አሰራር ሥርዓትን (Deliverology) ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ የማስፈፀሚያ ስልትና የባለድርሻዎች ሚና ምን እንደሚመስል በሰፊው ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የሥነ ዜጋና የሥነ-ምግባር ትምህርት ስኬቶች፣ ክፍተቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ምን እንደሆኑ እና በጥልቅ ተሃድሶ ወቅት የተለዩ ችግሮች፣ የተቀየረው ሁኔታና ቀሪ ስራዎችን በተመለከተም በዩኒቨርሲቲው መምህራን የመወያያ ጽሑፉ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ከዚህ በመቀጠልም ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ምን ያህል እንዳወቁ ለመገምገም የሚፈተኑትን ማጠቃለያ ፈተና (Comprehensive exit exam) በተመለከተም ገለፃ ተደርጐላቸዋል፡፡

ለአዲስ ተማሪዎችም በተለየ መልኩ ስለ ሴኩላሪዝም ምንነትና የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ያለውን ገጽታ በተመለከተ ጽሁፉ በሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጐበታል፡፡ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው የ2ዐዐ9 ዓ.ም.አፈፃፀም እና የ2ዐ1ዐ ዓ.ም. ዕቅድም ለነባርና አዲስ ተማሪዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡ ከውይይቱ በኋላም የተለያዩ ጥያቄዎች በተማሪዎች ተነስተው በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥባቸዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በተለያዩ ኘሮግራሞች እየሰጠ ሲሆን ከመደበኛ ተማሪዎች በተጨማሪ አዲስ ለሚገቡ የማታ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ክፍሎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን፣ የዩኒቨርሲቲውን ህጐችንና ደንቦችን በተመለከተ ገለፃ በማድረግ የቅድመ ትውውቅ ስራ ሰርቷል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .