ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂክ ዕቅድ ነደፈ

  • -

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂክ ዕቅድ ነደፈ

Print Friendly, PDF & Email

 

ስትራቴጂክ ዕቅዱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓትን በመቀየስ የሠራተኞችን ሥነ-ምግባር በመገንባት ሙስና እንዳይፈም የመከላከል ብሎም ተፈፅሞ ሲገኝ ተጠያቂነት እንዲኖር የማድረግ ዓላማ አለው፡፡  የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ጎጃም አበበ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች ባቀረቡበት ወቅት የሙስና ወንጀል ምንነት በመረዳት የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች በመለየት የመከላከል ዓበይት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ስትራቴጂክ ዕቅዱ እስከ 2012 ዓ.ም ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በቅድመ መከላከል ሥራ ላይ ትኩረት ይሰጣል፡፡ የመከላከል ሥራውን ስኬታማ ለማድረግም በየደረጃው ከሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንደሚፈጥሩም ገልፀዋል፡፡

ሁሉም የሥራ ክፍሎች የሙስና መከላከል ስትራቴጂክ ዕቅዱን ከመደበኛ ዕቅዶቻቸው ጋር በተቀናጀ መልኩ በማቀድ ወደ ተግባር እንዲገቡ የበላይ አመራሩ መመሪያ በመስጠት፣ አፈጻጸሙን በመቆጣጠርና መመሪያውን ተከትሎ አገልግሎቱን በመስጠት የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ጎጃም አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ከዳይሬክቶሬቱ ጋር በቅርበት የሚሰራ የሙስና መከላከልና ሥነ-ምግባር ካውንስል መቋቋም እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሚታየውን የሙስናና ሃብት ብክነት አካባቢዎች ተለይተው የስጋት ትንታኔዎች በመድረኩ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት ስትራቴጂክ ዕቅዱ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚከሰት ሙስና፣ በግዥ፣ በፋይናንስ፣ በንብረት አስተዳደርና በሌሎች መስኮች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት ተብራርቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሙስና አዝማሚያዎች የሚታዩ ሲሆን የውስጥ አሰራር መመሪያና ማንዋል አለመኖር እንዲሁም የክትትልና ቁጥጥር ክፍተት መኖር እንደምክንያት ሆነው በመድረኩ ተነስተዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ የተቀናጀ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂክ ዕቅዱ በቅድመ መከላከል ሥራ ላይ ትኩረት ስለሚያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ሁሉም የዩኒቨርሲቲው አካል የየድርሻውን ሃላፊነት መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ መንግስት የሚፈልገው ዩኒቨርሲቲዎች አሰራራቸውን በማስተካከል ለሌሎች ሞዴል እንዲሆኑ ስለሆነ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን ሞዴል ለማድረግ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በመረባረብ እየታየ ያለውን ሙስና ለማስቀረት ዘብ መቆም እንዳለበትም ጥሪ አስተላልፏል፡፡ ስትራቴጂክ ዕቅዱ በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች፣ ሃላፊዎችና ተማሪዎች ዘንድ ተፈፃሚ እንደሚሆንም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .