የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣የህግ ትምህርት ቤት እና የመሬት አስተዳደር ተቋም በጋራ አመታዊ የምርምር ጉባኤ አካሄዱ፡፡

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣የህግ ትምህርት ቤት እና የመሬት አስተዳደር ተቋም በጋራ አመታዊ የምርምር ጉባኤ አካሄዱ፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመበት ሶስት ተልዕኮ  አንዱ ችግር ፈች ጥናትና ምርምር  ማድረግ ነው፡፡ ሆኖም የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ሶስተኛውን አገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤ አካሂዷል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት  ረዳት ፕሮፌሰር ገነት ደጉ በመክፈቻ ንግግራቸው “ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች  ሲቋቋሙ ሶስት አላማዎችን  መነሻ በማድረግ ከዚህ ውስጥ ችግር ፈች ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣ ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችንና የአካባቢውን የመልማት አቅምና ጸጋዎችን ተጠቅሞ አካባቢውን ብሎም ክልሉን ከዚያም ሀገሪቱን ወደ ተሻለ  ነገር ለማሻገር  ታስቦ ነው”  ብለዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታው ጀምሮ ለጥናትና ምርምር ልዩ ትኩረት በመስጠት በአሁኑ ሰዓት እንደ ተቋም በምርምሩ ስራ ጥሩ እንቅስቃሴ አለ ሆኖም ባለፈው አመት  የኮሮና ቫይረስ በሽታ አቋርጦን ነው እንጅ ብዙ የምርምር ስራዎች ይሰሩ ነበር ነገር ግን  ዘንድሮ የምናከብረው የምርምር ጉባኤ 11ኛው ሲሆን  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ  ጥናትና ምርምሮች እየጨመሩ በመምጣታቸውና ወደ ኮሌጆች ወቅታዊና አነጋጋሪ ጉዳዮችን እየለዩ ጉባኤዎችን እንዲያዘጋጁ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት  የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ 3ተኛው ጉባኤ ሲሆን ለህግ ት/ቤትና ለመሬት አስተዳደር ደግሞ የመጀመሪያው ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

የኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ  መምህር  በልስቲ ወዳጄ  ያቀረቡት ጥናታዊ ጹሁፍ  የአለም አቀፍ የሂሳብ አሰራር መርሆዎች  በአገራችን እንዴት ይተገበራሉ የሚል ሲሆን የአለም አቀፍ የሂሳብ ስታንዳርድ በምንጠቀምበት ጊዜ ተቋማት ምን አይነት ችግር ያጋጥማቸዋል የሚል ጥናት ቀርቧል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር አሸብር ጸጋየ እንደገለጹት የኮሮና ቫይረስ በሽታ በጥቃቅንና አነስተኛ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ለማሳየት ነው፡፡

ጥናቱ በአሁኑ ሰዓት አለማችንና ሀገራችን በኮሮና ቫይረስ እየተጠቃ ሲሆን አብዛኛው ጥቃቅንና አነስተኛ የሚባሉት የስራ ዕድል ፈጠራ እንደሚሰሩ በጥናቱ ለማሳየት ተሞክሯል ብለዋል፡፡

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይህይስ አረጉ  በማጠቃለያ ሀሳባቸው እንደተናገሩት ስንማር የተማርነው አንድም ለመመራመርና  ለማስተማር፣ ለማሰልጠንና ለማማከር የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ነው ሆኖም የሁለቱ ቀን ስብሰባ ግብርና ላይ ቢዝነስ ኢኮኖሚክስና ሶሻል ሳይንስ ላይ በደንብ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡

Print Friendly, PDF & Email

Photo Gallery

DMU Radio Broadcasting . . .