የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ተቋም በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመክፈት የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ አካሄደ፡፡

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ተቋም በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመክፈት የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ አካሄደ፡፡

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመበት ሶስት አላማዎች አንዱ በመማር ማስተማሩ ዘርፍ የትምህርት ፕሮግራሞችን ማስፋፋት ነው፡፡ ይህን ዓላማ እውን ለማድረግም በሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የተለያዩ አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞችን  በመክፈት  በትጋት  እየሰራ  ይገኛል ፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ተቋም የሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል ተጠሪ  አቶ ተመስገን አደመ እንደተናገሩት የቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ  በ2014 ዓ.ም በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ  በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሂዷል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ተቋም  የሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል መምህር  ዶ/ር ተሰራ ቢተው እንደገለጹት “በሁለተኛ ዲግሪ የሚከፈቱ ፕሮግራሞች  ቅድመ ልጅነት ሳይኮሎጂ፣ ዴቨሎፕመንታል ሳይኮሎጂ እና  ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ ሲሆኑ የሥርዓተ ትምህርቱ ግምገማ ለሴኔት እንዲቀርብ ተደርጎ ውሳኔ እንዲያገኝ ይደረጋል” ብለዋል፡፡  

በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመክፈትም የዳሰሳ ጥናት የተሰራ ሲሆን  ከዚህ በፊት ሥርዓተ-ትምህርቱ በትምህርት ክፍል ደረጃና በኮሌጅ ደረጃ እንዲገመገም ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ከጅማ ዩኒቨርሲቲና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጡ ተጋባዢ እንግዶች እየተገመገመ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

“በመሆኑም ፕሮግራሙን  ለማስጀመር  ዩኒቨርሲቲው፣ ኮሌጁ፣ ብሎም ዲፓርትመንቱ  ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Print Friendly, PDF & Email

Photo Gallery

DMU Radio Broadcasting . . .