በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሐዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም የምርምር ትልመ ጥናት ተቋቁሞ (Proposal Defense) አካሄደ

  • -

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሐዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም የምርምር ትልመ ጥናት ተቋቁሞ (Proposal Defense) አካሄደ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሐዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም ለ2ዐዐ9 ዓ.ም. በተለዩ የጥናትና ምርምር የትኩረት መስኮች (Thematic Areas) በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪዎች በተሠሩ የምርምር ትልመ ጥናቶች ላይ ተቋቁሞ ተካሂዷል፡፡

የሐዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው አንዳርጌ እንዳሉት ተቋሙ በ2ዐዐ9 በጀት ዓመት በተለዩ የጥናትና ምርምር የትኩረት መስኮች የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪዎች ጥናትና ምርምር ሊያደርጉባቸው ያሰቧቸውን አምስት የምርምር ትልመ ጥናቶች ለታዳሚዎች አቅርበው ውይይትና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በተቋሙ በተቀመጠው የጥናትና ምርምር የትኩረት አቅጣጫ መሰረት ጥናት ለማድረግ ትልመ ጥናት ካቀረቡት መካከል “Innovation and Communication in the Business Performance of Indigenous Cultural Industries: The case of weaving, Tannery and Pottery Industries in Gojjam” በሚል ርዕስ እነ ረዳት ፕሮፌሰር ወንድይፍራው ምህረት ሊያጠኑ መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህ ጥናትም ህብረተሰቡ በእደ ጥበብ ሙያው ምን ያህል  እየተጠቀመበት እንደሆነ፣ የሚሰሯቸው ስራዎች በገበያ ላይ ያላቸው ተፈላጊነት ምን ያህል እንደሆነና ከበፊቱ ጋር ያለው ልዩነት ምን እንደሚመስል ሊዳስስ እንደሚችል ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ “ጨንገር የመያዝ ልማድ በምስራቅ ጐጃም” በሚል ርዕስ እነ ዶ/ር ደመቀ ጣሰው  ባቀረቡት ትልመ ጥናት ለማየት እንደተቻለው ጥናታቸው የሚያተኩረው ጨንገር የመያዝ ልማድ በምስራቅ ጐጃም ዞን ያለውን ባህል በተመለከተ እና ለምን ፋይዳ እንደሚጠቀሙበት ሲሆን ጥናቱም የአካባቢውን ባህል፣ ወግና ልማድ ያስተዋውቃል ተብሎ ይገመታል፡፡

በአጠቃላይ በሀዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም ለጥናትና ምርምር በዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪዎቹ የምርምር ስራ ለመስራት የቀረቡት ትልመ ጥናቶች የአካባቢውን ባህል ለማስተዋወቅ፣ ለመጠበቅ እና ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚኖራቸው ሚና የጐላ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመጨረሻም እነዚህ ትልመ ጥናቶች በአምስት አጥኚ ቡድኖች ቀርበው እያንዳንዳቸው ስለ አላማው እና ጠቀሜታው በአቅራቢዎች ሰፊ ማብራሪያ ከተሰጣቸው በኋላ በታዳሚዎችም የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ለጥያቄዎቹም የትልመ ጥናት አቅራቢዎቹ  መልስና ሰፊ ማብራሪያ ሲሰጡ ታዳሚዎቹ በእያንዳንዱ አጥኚ ቡድን ለቀረቡት ትልመ ጥናቶች ሊሻሻሉና ሊጐለብቱ የሚገቡ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

Print Friendly, PDF & Email

Search DMU

DMU Radio Broadcasting . . .