የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የሞዴል ፋርማሲ ማቋቋሚያ ወርክሾፕ አዘጋጀ፡:

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የሞዴል ፋርማሲ ማቋቋሚያ ወርክሾፕ አዘጋጀ፡:

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመባቸውን ሶስት ተልዕኮዎች አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞችን በመክፈት የመማር ማስተማሩን ስራ በትኩረት በመስራት ለአካባቢው ማህበረሰብ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ሆኖም የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከአጋር አካላት ጋር  በመተባበር የሞዴል ፋርማሲ ለማቋቋም ፕሮፖዛል አቅርቧል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን  ግርማ አለም  በመክፈቻ ንግግራቸው   “በፋርማሲ ትምህርት ክፍል ተነሳሽነት  የመድሃኒት  ቤት ለማቋቋም  የተቀረጸ  ፕሮጀክት ሲሆን ይህ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ውይይት የተደረገ ሆኖ ለመማር ማስተማሩ  ስራ ግብዓት  ስለሚሆን ተማሪዎች የተግባር ትምህርት ይማሩበታል፣ መምህራንም ዕውቀታቸውን ያዳብራሉ፣ መድሃኒትም ከመሸጥ ባለፈ ሌሎችን የመድሃኒት አይነቶች የማምረትና ለማስተማሪያ እንዲሆኑ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል፡፡ ለከተማው ማህበረሰብም  በተመጣጣኝ ዋጋ መድሃኒት ለማቅረብና ተጠቃሚ ለማድረግ ሊቋቋም የታሰበ ፕሮጀክት ነው” ብለዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤናሳይንስ ኮሌጅ ፋርማሲ ትምህርት ክፍል መምህር አንተነህ በላይነህ የቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ አላማ በከተማችን ላይ ሞዴል ፋርማሲ ለማቋቋምና ከሌሎቸ በተሻለ መልኩ በጥራትና ብዛት  የመድኃኒት ማደያ  መድኃኒት ቤት  ለማቋቋም ነው፡፡ ብዙ ጊዜ  በከተማችን ውስጥ መድሃኒቶች ከሆስፒታልና ከግል ተቋማት ይጠፋሉ፡፡ ስለሆነም  ይህን ችግር ለመፍታት ሙሉ ለሙሉ የግል ፋርማሲዎችን ከገበያ በማስወጣ መንገድ  ማህበረሰቡን ለማገዝ  የሚጠቅም ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ አስፈላጊ የሚባሉ መድሃኒቶችን ከማቅረብ አንጻር  እንደ ግፊት፣ ስኳር፣  በሽታዎች የመድሃኒት እጥረት ስላለ  በብዛት እንዲቀርብ ማድረግና ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ረግድ ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን የወርክሾፑ ተሳታፊዎች የገለጹ ሲሆን በመጀመሪያ ፕሮፖዛሉን ላዘጋጁት ለፋርማሲ ትምህርት ክፍል ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደርጃው ፈንቴ ይህን ፕሮጀክት ለመጀመር እቅዱ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን የቢዝነስ እቅዱ ሰፋ ያለ ስለሆነ እንደገና ክለሳና ማስተካከያ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል፡፡  የዚህ ሞዴል ፋርማሲ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መቋቋም  ለደብረ ማርቆስ ከተማ ማህበረሰብ  ያለውን የመድሃኒት እጥረት ችግር እንደሚፈታም አስረድተዋል፡፡  ለፋርማሲ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችም ከጽንሰ-ሃሳብ ትምህርት ባለፈ ለተግባር ትምህርት ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

Print Friendly, PDF & Email

Photo Gallery

DMU Radio Broadcasting . . .