ጃፓይኮ(JHPIEGO) ኢትዮጵያ ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሎጅ (SMART Class Room) ለማቆቋም የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

  • -

ጃፓይኮ(JHPIEGO) ኢትዮጵያ ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሎጅ (SMART Class Room) ለማቆቋም የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ደ/ማ/ዩ፡- በደብረ ማርቆስ የኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ አለም እንደገለጹት ጃፓይኮ(JHPIEGO) ኢትዮጵያ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ለደብረ ማርቆስ የኒቨርሲቲ ለጤና ሳይንስ እና ለግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጆች የሙያና የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ ያለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ነዉ፡፡

JHPIEGO)ኢትዮጵያ ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያደረገዉ ድጋፍ

በጃፓይኮ(JHPIEGO) ኢትዮጵያ በስነ-ምግብ (Senior Program) መኮንን ወይዘሮ ሀገሬ አለሙ በበኩላቸዉ ጃፓይኮ(JHPIEGO) በኢትዮጵያ የአምስት አመት ፕሮጀክት በመቅረጽ ከ2016 -2021ዓ.ም ድረስ ለሃያ ዘጠኝ ተቋማት ድጋፍ ሲያደረግ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ነዉ፡፡ ለዚህም ስኬት ከላይ እስከ ታች ያለዉ የዩኒቨርሲቲው አመራር ቀናነትና ስራ ወዳድነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስነ-ምግብ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ባያቸዉ አስማረ አጠቃላይ ጃፓይኮ (JHPIEGO) ኢትዮጰያ ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያደረገዉን ድጋፍ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በገለጻቸዉም ስርዓተ-ትምህርት ክለሳ፣ የአቅም ግንባታና የተለያዩ የክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠትና የትምህርት ጥራት ለማሳድግ በሚደረገዉ ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

በመጨረሻም ጃፓይኮ (JHPIEGO) ኢትዮጵያ ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ላደረገዉ ድጋፍ የምስጋና መልዕክት ከተላለፈ በኋላ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቤተ ሙከራ ተጎብኝቷል፡፡

Print Friendly, PDF & Email

Photo Gallery

DMU Radio Broadcasting . . .