ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ግቢ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፓሊሲና ስትራቴጂ፣ የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድና ቁልፍ የዉጤት አመላካቾች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

  • -

ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ግቢ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፓሊሲና ስትራቴጂ፣ የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድና ቁልፍ የዉጤት አመላካቾች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

ደ/ማ/ዩ (መጋቢት፣ 2013 ዓ.ም)፡- በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፓሊሲና ስትራቴጂ፣ የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድና ቁልፍ የዉጤት አመላካቾች “የጠራ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ፓሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ የልማት ዕቅድና ፕሮግራሞች ለሁለንተናዊና ዘላቂ ሀገራዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ መጋቢት 13/07/2013ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በዕለቱም የስልጠናዉ ዓላማ እና አካሄድ ላይ አጭር ገለጻ ከተደረገ በኋላ በከፍተኛ ትምህርት ፓሊሲና ስትራቴጂዎች፣ የሳይንስና ፖሊሲ ስትራቴጂዎች፣ የከፍተኛ ትምህርትና የሳይንስ ልማት የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ እና ቁልፍ አመላካቾችና የደብረ ማርቆስ የኒቨርሲቲ የአምስት አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የሚሉ ሰነዶችን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲተ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ይሄይስ አረጉና የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ሞላልኝ ታምሩ አቅርበዋል፡፡

ስቀረቡት  ሰነዶችና  ስለ ዉይይቱ አጠቃላይ ይዘት የቡሬ ግቢ ዲን  ዶክተር ጸበሉ አባይነህን አናግረናቸዉ የሚከተለዉን ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ ስልጠናዉ በከፍተኛ ትምህርት እና በሳይንስ ልማት በተያያዘ በተደራሽነት፣ በጥራት፣ አግባብነትና ፍትሐዊነት የተሰሩ ሰራዎች ሀገሪቱ መመለስ ካለባት ጥያቄዎች አንጻር ጎላ ያሉ ክፍተቶች እንዲሁም ከመሰረተ ልማት ጋር የተየያዙ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡

በተጨማሪም  በስልጠናዉ እንደ ትልቅ ነጥብ ሆኖ የተነሳዉ ለራስ ትኩረት በመስጠት በሀገር በቀል እዉቀትና በፈጠራ ስራ ላይ  እየተሰራ ያለዉ ስራ በአፈጻጸም ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የራስን ችግር ለመፍታት ማነቆ እንደሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ከበፊት ያልተፈጸሙ ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አሁን ላይ ተግዳሮት እንደሆኑ፤ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት የሳይንስና ልማት የአስር ዓመታት መሪ ዕቅድና ቁልፍ የዉጤት አመላካቾች መሰረት ያደረገ  የአምስት አመት ስትራቴጂ ዕቅድ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንን፤ ከዚህም በመነሳት የቡሬ ግቢ የራሱን ዕቅድና ስትራቴጂ ማዘጋጀቱ ተገልጧል፡፡

 በመጨረሻም ስልጠናዉ ሁሉም ፈጻሚ አካላት እንደ አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሰራተኞች የከፍተኛ ትምህርት ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የወደፊት የልማት ዕቅዶች ላይ የጠራ ግንዛቤ ፈጥሮላቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸዉ  በመግለጽ ሃሳባቸዉን አጠቃለዋል፡፡


Print Friendly, PDF & Email

DMU Radio Broadcasting . . .