GROW WISER AT THE WATER TOWER
Staff Academic Administrative Graduate
የአገራችን የግብርና ዘርፍ ባለፉት ዓመታት ችግሮችን የመቋቋም አቅም የገነባ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በመንሸራትት ላይ መሆኑ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ የመቋቋም አቅም ገንብቷል የሚያሰኘው ለዘመናት ባልተቀየረ የማረሻ መሳሪያና የአስተራረስ ስልት በማደግ ላይ ያለውን የአገሪቱን ሕዝብ ቁጥር የመመገብ ግዴታውን በመወጣት ላይ መሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከ10 ሽህ ዓመታት በፊት በኒዮሊቲክ አብዮት ዘመን ጀምሮ የበርካታ የአዝእርትና እንስሳት ሀብት30
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ የሚያከናውናቸው የተለያዩ የልማት ስራዎችና ፕሮጀክቶችን የዩኒቨርሰቲዉ የማኔጅመንት አባላት ፣ የኮሌጅ ዲኖች እና ዳይሬክተሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እና የአካባቢዉ ማህበረሰብ በተገኙበት መጋቢት 10/2014ዓ.ም የመስክ ጉብኝት ተደርጓል፡፡ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ቡሬ ካምፓስ ካለዉ የመልማት አቅም አንጻር በሚፈለገዉ ደረጃ ያልተሰራበት ነገር ግን ጅምሩ የሚበረታታ30
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል በዋግኽምራ ዞን አሸባሪው ህውሃት በከተፋው ጦርነት ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን ድጋፍ ለማድረግ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች መልሶ ለመገንባት ለማቋቋም የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በዚሁ ዞን ተፈናቅለው በሰቆጣ ከተማ የድረሱልን ጥሪ እያስተጋቡ ለሚገኙ እናቶች፣ ህፃናትና አረጋዉያን ዩኒቨርሲቲው ድጋፉን30
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ከባሕርዳር እስከ ደብረ ማርቆስ ድረስ ባለው መንገድ መዳረሻ ላይ በስራ ፈጣሪዎች የገቢያ ትስስርና የባለድርሻ አካላት የግንኙነት ክፍተት ትንተና እና ንግድን ማዕከል ያደረገ ስራ ፈጠራ ዙሪያ አውደ ጥናት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቡሬ ከተማ ተካሂዷል፡፡ መርሃ-ግብሩን በንግግር የከፈቱት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ እንደገለጹት በየዓመቱ30
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 126ኛውን የአድዋ ድል በዓል ‹‹አድዋ ለኢትዮጵያውያን ህብረት ለአፍሪካውያን የነጻነት ጮራ ›› በሚል መሪ መልዕክት በንጉስ ተክለሃይማኖት አደባባይ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የሐዲስ ዓለማየሁ የጉባዔ አዳራሽ በፓናል ውይይት ተክብሯል፡፡ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት አድዋ የኢትዮጵያ የዘመናት የድል ብስራት ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ሃውልት ጭምር ነው፡፡ ሆኖም30
የዛሬዋ ዓለማችን በደረሰችበት የእድገት ደረጃ ስልጣኔን ወይም ብልጽግናን ከቴክኖሎጂ ለይቶ ማየት ያስቸግራል። የሰለጠነ ህብረተሰብ ማለት ቴክኖሎጂን ያዳበረ ህብረተሰብ ማለት ነው። ባንጻሩም ቴክኖሎጂን ያላዳበረ ህብረተሰብ ማለት ደግሞ ያልበለጸገ ህብረተሰብ ነው። የሰለጠነ ህብረተሰብ ስንል ደግሞ ድኅነት የተረታበት፤ በሽታ የመነመንበት፤ ትምህርት የተስፋፋበት (እውቀት የለመለመበት)፤ ዲሞክራሲ የሰፈነበት፤ የመገናኛና ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በስፋት የተንሰራፋበትና ህግ የበላይ የሆነበት ህብረተሰብ ማለታችን ነው።30
@DMU
DMU Radio Broadcasting . . .