የሃዲስ ዓለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም‹‹ከሳጠራው ግርጌ›› በሚል ርዕስ የተጻፈ መፅሐፍ አስመረቀ

ደ/ማ/ዩ፡-ሃዲስ ዓለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም በደብረ ማርቀስ ዩኒቨርሲቲ የትያትር ጥበብ መምህር በሆኑት አቶ ደሳለኝ ቀጸላ የተጻፈው ከሳጠራው ግርጌ የተሰኘ መፅሐፍ በድምቀት አስመረቀ፡፡
በመፅሐፍ ምረቃው ወቅት የተገኙት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ መጽሀፍ ጽፎ ለህዝብና ለአንባቢያን ማድረስ ከዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ያለበት አካባቢ እንደ እነዚህ አይነት ተሰጥዖ ያላቸው ግለሰቦች መፍለቂያ እና የስነ-ጽሁፍ አካባቢ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲው ተግባር እንደዚህ ዓይነት ሥራዎችን ማገዝና ማበረታታት ነው፡፡
ለዚህም የሃዲስ ዓለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም የመፅሐፍ ምረቃና የኪነጥበብ ምሽት እያዘጋጀ በርካታ ጀማሪ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ዶ/ር ታፈረ ገልጸዋል፡፡ይህንን መፅሐፍና ተጨማሪና ትልልቅ ሃሳቦችን በማውጣት እየሰሩ መጓዝ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ በወቅቱም የመምህር ደሳለኝ ቀጸላን የግጥም መድበል የመረቁ ሲሆን ደራሲው ከዚህ የበለጡ በርካታ ሥራዎችን በመስራት ለተደራሲያን እንደሚያደርሱ ተስፋ እንዳላቸው ዶ/ር ታፈረ ገልጧል፡፡
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህረሰብ አገልገሎት ም/ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ገነት ደጉ በበኩላቸው የመፅሐፍ ምርቃውን እውቅና በሚሰጡበት ወቅት ሀዲስ አለማየሁ ከያዛቸው ተልዕኮዎች መካከል ተዘጋጅተው የቀረቡ የመጻፍ ምረቃ ስነ-ስርዓት ባለሙያዎችንእውቅና ለመስጠትእንደሆነ ገልጸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የመጣውን የንባብ ባህላችንን እና አስተሳሰባችንን ተቋቁሞ ባልተመቻቸ ሁኔታየተሰሩ ስራዎችን ለማሳደግ ‹‹ከሳጠራው ግርጌ›› የተሰኘው መፅሐፍ በእለት ከዕለት ተግባራችን የምኖረውን ህይወት የሚዳሰስ በመሆኑ ሁሉም ስራተኛ የራሱ ሊለው ይገባል ብለዋል፡፡
በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የሥነ-ፅሁፍ መምህር የሆኑት ዶ/ር ደመቀ ጣሰው ከሳጠራው ግርጌ የተሰኘውን የግጥም መድብል ላይ ባደረጉት የይዘት ዳሰሳ ሳጠራ ግድግዳ ወለል፣ ጣራ፣ ግድግዳ፣ የእንጀራ መመገቢያ፣ የእንጀራ መሳቢያ የሚል ትርጉም ሲኖረው በቀላል የአቀራረብና የቀረበ ሃሳባዊ ግንኙነት የተሰጠ የባለሀብቱን ህይወት የሰሪውን ህይወት፣ ትግስት፣ ተስፋ፣ ምኞት፣ የዳሰሰ ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የግጥም መድብሉ ቅርፅ፣ ቃላት መረጣ፣ ሳቢነት፣ ትርጉም ያለው መልዕክቶች በመጠቀማቸው ገጣሚው የዘመኑን ህዝብ በፈጣንነት የታጀቡ መልካም ርዕሰ ጉዳይ እና ተጨባጭ ጭብጥ የያዘ ፍቅር፣ አገር፣ ፖለቲካ፣ ስደት፣ ህይወት፣ ማህበረሰብ፣ ለተደራሲው ማህበረሰብ የንባብ ፍላጐት ጥማትን በማርካት ዙሪያ ገበያውን የመረመረ ስርዓት ሲሉ ሙያዊ ዳሰሳቸውን አቅርበዋል፡፡
በፕሮግራሙ የግጥም፣ መነባንብ፣ ቅኔና ተዛማጅ የመዝናኛ ፕሮግራሞች በተለያዩ አካላት ቀርበዋል፡፡