ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለሥራ ፈላጊ ወጣቶች የሥራ ፈጠራ ሥልጠና ሠጠ

የደ/ማ/ዩ፡- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከምስራቅ ጐጃምዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ጋር በመተባበር በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ለተዉጣጡ 63 ሥራ ፈላጊ ወጣቶች በሥራ ፈጠራ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራ ማዕከል ኦፊሰር የሆኑት አቶ ፈንታሁን አየነዉ  ስልጠናዉ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዉ ስራ ፈላጊ ወጣቶች እንዴት ተደራጅተዉ እንደሚሰሩ፣ዉጤታማ እንደሚሆኑ፣ የገንዘብ አያያዛችዉ ምን መሆን እንዳለበትና ሥራ ያልጀመሩ ወጣቶች ደግሞ እንዴት ስራ ፈጥረዉእንደሚሰሩ የሚጠቅም ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ ዬሐንስ ገብረ ማሪያም የሥራ ፈጠራ ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ የንግድ ስራ ባህርያት፣ ስራ ለመጀመር የሚስፈልጉ ነገሮችላይ ትኩረት በማድረግ ስልጠናዉን ሠጥተዋል፡፡

የስልጠናዉ ተሳታፊዎችም በበኩላቸዉ ከዚህ በፊት ያልተደራጁ እና ስራ ፈጥረዉ በአዲስ ለሚሰሩ ወጣቶች ስለ ስራ ፈጠራ ምንነት፣ ስለ ገንዘብ አያያዝ እና ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል የተሰጠው ስልጠናሰፊ የሆነ ግንዛቤ ከስልጠናዉ ማግኘቱን ተናግሯል፡፡

በመጨረሻም ከተለያዩየስራሃላፊዎች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በስራ ፈጠራ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችንና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በሚመለከት ተጨማሪ ዉይይት ተካሂዷል፡፡