
የ/ደ/ማ/ዩ፡-የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአይሲቲ ትምህርት ክፍል በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚገኙ ቴክኒክና ሙያ መምህራን ስለ ጆኦግራፍያዊ የመረጃ ስርዓት (ጄአይኤስ) ሶፍትዌር መረጃን ለማያዝ፣ ለማከማቸት፣ ለማስተዳደር፣ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ሂደቶችና ዘዴዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናዉ እንደተገለጸዉ የጆግራፊያዊ መረጃ ስርዓት መረጃን ለመያዝ፣ ለማከማቸት እና ለማስተዳደር በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያዎች ዘንድ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለ ተጠቅሶ ይህንን ክፍተት ለመሙላት የጄአይኤስ ሶፍትዌር ስልጠና ለመስጠት እንዳስፈለገ ተገልጻል፡፡
ሰልጣኞች ጄአይኤስ ሶፍትዌር በስልጠናዉ ባገኙት ዕዉቀትና ክህሎት መሰረት የጆግራፊያዊ መረጃ ስርዓት ያለባቸዉን ክፍተት ይሞላሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡
ስልጠናዉን ከሰጡት አሰልጣኞች መካከል በደብረ ማርቆስ ዪኒቨርስቲ ቴከኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሃይድሮሊክና የዉሃ ምህንድስና መምህር የሆኑት አቶ በእዉቀቱ አሰፋ በተሰጠዉ ስልጠና ዙርያ በሰጡት አስተያየት የጆግራፊያዊ መረጃ ሶፍትዌር ስልጠናዉን የተሰጣቸዉ መምህራን ለሚያስተምሯቸዉ ተማሪዎች የተሟላ እዉቀት እና ክህሎት እንዲኖራቸዉ ሶፍትዌሩ ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡ሰልጣኖቹ በተሰጣቸዉ ስልጠና ደስተኛ ሆነው በከፍተኛ ተነሳሽነት ስልጠናዉን እንደሰለጠኑ በመግለፅ ለወደፊትም ስልጠናዉ ቀጣይነት ይኑረው በማለትአስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
አቶ ግሩም አድነዉ ከየጁቤ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የመጡ ሰልጣኝ ሲሆኑ በሰጡት አስተያየት የጅአይኤስ ሶፍትዌር አጠቃቀም ደብረማርቆስ ዪኒቨርስቲ ስልጠና ማዘጋጀቱ አስፈላጊ እንደሆነና ስልጠናዉ ክፍተቱን እንደሞላላቸዉ ጠቅሰው በስልጠናዉ ያገኙትን እዉቀትና ክህሎት ለሚያስተምሯቸዉ ተማሪዎች እንደሚያካፍሏቸዉ ገልፀዋል፡፡
