
ደብረ ማርቆስና ወሎ ዩኒቨርሲቲዎች በትብብር የአርበኛ በላይ ዘለቀን የአርበኝነት ተጋድሎ ለመዘከር
በሚዘጋጀዉ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤና ታሪካዊ ጉዞ በተመለከተ በአማራ ክልል የሚገኙ አስሩ ዩኒቨርስቲዎች የሚሳተፉበት ወርክሾፕ ተካሄደ፡፡
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘደንት ረዳት ፕሮፌሰር ገነት ደጉ የወርክሾፑ ዋና አላማ የአርበኛ በላይ ዘለቀን የ75ኛ አመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ አለማቀፍ ጉባኤና ታሪካዊ ጉዞ ለማዘጋጀት በሚኖረው ሂደት ውስጥ ምን መምሰል አለበት የሚሉ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤና አቅጣጫ እንዲኖር ለማድረግ የተዘጋጀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የፕሮጀክቱን ትልም ያቀረቡት የታሪክ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ደርብ ተደራ የአርበኛ በላይ ዘለቀ የትዉልድ ቦታና የአርበኝነት ተጋድሎዉን እንዲሁም አርበኛዉን መዘከር ለምን እንዳስፈለገ ሲገልፁ በትውልድ ቅብብሎሽ መሃከል ሃገራዊ አንድነት እየተረሳ ስለሃገር የሚቆረቆር ዜጋ ማፍራቱ ላይ ክፍተቶች ስላሉ ያንን ክፍተት ለመሙላት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ፕሮፖዛል ላይ ከአማራ ክልል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና የተጋበዙ የታሪክ ምሁራን የተገኙ ሲሆን የሚኖረውን ዓለምአቀፍ ፕሮግራም አስመልክተው ሃሳብና አስተያየታቸውን በሂደቱና በተግባር ሰምሪቱ ላይ ሰጥተዋል፡፡
