
የደ/ማ/ዩ፡- የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረስብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከህግ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር ለዳኞች፣ ለዐቃያነ ህጎችና ለፖሊሶች የህግ ትግበራ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ የማህበረስብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ምህረት አለማየሁ በፍትህ አካላት ዘንድ ያለዉን ክፍተት ለመሙላት ስልጣናዉ አስፈላጊ እንደሆነአስረድተዋል፡፡
በስልጠናው የጉዳት ካሳ አወሳሰን እና የጉዳት ስሌት በተመለከተ የመነሻ ጹሁፍ የቀረበ ሲሆን በስራላይ የሚደርስ አደጋ የሰበር ውሳኔዎች፣የአሰሪው ኃላፊነት፣በስራላይ የሚደርስ አደጋትርጉም፣የጉዳት ካሳ አሰላል ከአሰሪና ሰራተኛ ከአዋጁ አንጻር ምን እንደሚመስል ተብራርቷል፡፡
እንዲሁም የህጻናት ወንጀለኝነት እድሜ አወሳሰንና ዉጤቱ በአለም አቀፍና በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል የመነሻ ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን በፅሁፉ የህፃናትጉልበት ብዝበዛ ምንነት፣የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ አይነቶች፣የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ መንስኤዎች ፣የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ የሚያስከትለው ጉዳት፣የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን የሚመለከቱ የህግ ማእቀፎች በዝርዝር ተዳሰዋል፡፡
የህጻናት ክርክር በፍትህ ተቋማት ያለዉ ሚና (በፖሊስና በፍ/ቤቶች) የመነሻ ጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በጹሁፋቸዉም የህጻናት ማሳደጊያ ተቋም ትከሚሰጧቸው የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎቶች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች እንዲሁም የህጻናትን የህግ ከለላ ከፍትሐ ብሄር ህግ አንጻር ምን እንደሚመስል ተብራርተዋል፡፡
መረጃ አያያዝን በተመለከተም የመረጃ ምስጥራዊነት መርህ የመነሻ ጹሁፍ የቀረበ ሲሆን ስለመረጃ ምስጥራዊ አስፈላጊነት ሰለወሳኝ የመረጃ ምንጮች እንዲሁም የመረጃ ክፍተት ስለሚኖረዉ ተጽዕዖ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በስልጠናው የተሳተፉ ዳኞች፣ አቃቢያን ህጎችና ፖሊሶች በስልጠናው ይዘት በርካታ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዳገኙበት ተናግረዋል፡፡
