የዩኒቨርሲቲው ስራ ክፍሎች የ2013ዓ.ም በጀት አመት ዕቅድ አፈጻፀም ፣የ2014 በጀት አመት ዕቅድ ትውውቅና ግምገማ አደረገ

  • -

የዩኒቨርሲቲው ስራ ክፍሎች የ2013ዓ.ም በጀት አመት ዕቅድ አፈጻፀም ፣የ2014 በጀት አመት ዕቅድ ትውውቅና ግምገማ አደረገ

 

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳይ ዘርፍ የቡሬ ካምፓስ ጨምሮ በ28/01/2014 ዓ.ም ጀምሮ በንግስት ሳባ ሁለገብ አዳራሽ፣ የአስተዳደር ጉዳይ ዘርፍ ደግሞ በ29/01/2014 ዓ.ም ጀምሮ በአለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የ2013 በጀት አመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2014 በጀት አመት ዕቅድ ትውውቅ አድርገዋል፡፡

ዶክተር ይኸይስ አረጉ የአካዳሚክ ጉዳይ ምክትል ፕሬዚደንት በአካዳሚክ ጉዳይ ዘርፍ የተደረገውን የ2013 በጀት አመት የተከናወኑ የዕቅድ አፈጻጸምና የ2014 በጀት አመት ዕቅድ ትውውቅ ላይ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው የአስር አመት ስትራቴጅክ ዕቅድ የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ፣የደንበኞችና የአጋር አካላትን እርካታ በማሳደግ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችንን ጥራትና አግባብነት በማሸሻል የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በማጠናከር የቴክኖሎጅ ስራዎችን በልዩ ትኩረት በመፈጸም የዕቅድ አፈጻጸሙን ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የዕቅድ አፈጻፀም ግመምገማና ትውውቅ ከፊል ገጽታ

ዶክተር ሞላልኝ ታምሩ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት በአስተዳደር ዘርፍ የ2013ዓ.ም በጀት አመት የተከናወኑ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2014 በጀት አመት ዕቅድ ትውውቅ ላይ እንደተናገሩት የአስተዳደር ሰራተኞች የመማር ማስተማሩ እንዲሁም የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ፣ዉጤታማና ወጭ ቆጣቢ ሆኖ እንዲቀጥል የሚሰጡት ድጋፍ ሚናዉ የጎላ ስለሆነ በ2013 በጀት አመት የነበረዉን ጠንካራ ጎን በማስቀጠልና የነበሩትን ችግሮችን መቅረፍ እንዲሚገባ አሳስበዋል፡፡

በአካዳሚ ጉዳዮች ዘርፍና በአስተዳደር ጉዳዮች የቡሬ ካምፓስ ጨምሮ በ2013 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻፀም አጠቃላይ ግምገማ የተነሱ ጉዳዮች፣በዕቅድ አፈጻጸሙ የነበሩ መልካም ተሞክሮዎች፣ ጠንካራ ጎኖች፣ያጋጠሙ ችግሮች የተሰጡ መፍትሄዎች፣ ትኩርት የሚሹ ጉዳዮች፣ በ2014 በጀት አመት የዕቅድ ትውውቅ ላይ የተነሱ መነሻዎች ደግሞ የዕቅዱ ዓላማ፣ በዝግጅት ምዕራፍ የሚሰሩ ተግባራት በትግበራ ምዕራፍ ሚሰሩ ተግባራት፣ በማጠቃለያ ምዕራፍ የሚሰሩ ተግባራት ናቸው፡፡

የዘርፍ ስራዎች አዳዲስ እቅዶች መሪ የ10 አመቱን የኢትዮጵያ እቅድ ፣ የ10 ዓመቱን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ እቅድና ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች ያወረደውን መነሻ እቅድ ከግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆን በማሰብ ቀድመው የታቀዱትም ሆኑ አዳዲስ እቅዶች እንደገና እንዲታዪና ተጠቃለው በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ወጥ ሁኖ የሚፈጸም እቅድ ታቅዶ በየ በጀት ምዕራፉ እየተገመገመ የቅርብ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም የዩኒቨርሲቲው ተቀዋማዊ ለውጥና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .