GROW WISER AT THE WATER TOWER
Staff Academic Administrative Graduate
በዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ዶክተር ቴዎድሮስ በካፋ ስም የተሰየመው ይህ ግዙፍ ሕንፃ በዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ ከተገነቡ ትላልቅ ህንፃዎች አንዱ ሲሆን ህንፃው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የዩኒቨርሲቲያችን ሰራተኞች ያለባቸዉን የቢሮ ችግር ከመቅረፉ ባሻገር ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጡን ያሻሽላል ተብሎ ይታመናል፡፡
የሕንፃው ግንባታ ሰኔ 18 ቀን 2007 ዓ.ም ውል ተይዞ የተጀመረ ቢሆንም በግንባታ ስራ ተቋራጮች ደካማ የስራ አፈፃፀም፣ በግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መናር እና በሌሎችም የተለያዩ ምክንያቶች መጠናቀቅ ከነበረበት ጊዜ ዘግይቶ ተጠናቋል፡፡
የቴዎድሮስ በካፋ ሕንፃ ግንባታ ስራ ተደጋጋሚ የዉል ማቋረጥ ገጥሞት ነበር፡፡ ይሁን እንጅ በዩኒቨርሲቲያችን ማኔጅመንት የቅርብ ክትትልና ጠንካራ ዉሳኔ ተሰጥቶ ከፌደራል ግዥ ኤጀንሲ በማስፈቀድ በደብረ ማርቆስ ከተማ ለሚገኘውና የመንግስት የልማት ድርጅት ለሆነዉ መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ተሰጥቶ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ቀሪ የግንባታ ሂደቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅቷል። በዚህ አጋጣሚም የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ላሳየው የስራ ጥራትና ቅልጥፍና ማመስገን እንወዳለን።
There are no upcoming events.
DMU Radio Broadcasting . . .