የሰላም ፎረም ለመማር ማስተማር ሥራው ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ

  • -

የሰላም ፎረም ለመማር ማስተማር ሥራው ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ

Print Friendly, PDF & Email

 

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሠላም ፎረም የመማር ማስተማሩ ሥራ ውጤታማ እንዲሆን ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገለፀ፡፡ የፎረሙ ሠብሳቢ ተማሪ እሸቴ ምህረት እንደገለፀው የሠላም ፎረሙ የተቋቋመው በዋናነት በዩኒቨርሲቲው ውስጥና አካባቢ ሠላም እንዲሠፍን የግጭት መንስኤዎችን በመለየትና አለመግባባቶችን በመፍታት ችግሮች እንዳይከሠቱ የመከላከል ስራ በመስራት ችግሮች ሠላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት እንዲቻል መሆኑን አስረድቷል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሠላም ፎረም በግቢው ውስጥ ተገልጋይ ማህበረሠቦችን ቅድሚያ በማወያየት፣ የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት የመፍታት፤ መቻቻል እንዲሠፍን የማድረግ፣ የማስታረቅ፤ በዲሲፕሊን ምክንያት የሚባረሩ ተማሪዎችን ቁጥር የመቀነስ እና መሠል ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ እንዲሁም ከሌሎች አደረጃጀቶች ጋር በመቀናጀት የሠላም ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ ተግባራትን አስቀድሞ የመለየትና የመፍታት ስራ እንደሚሠራ ገልጿል፡፡

ፎረሙ ከተማሪዎች ከመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች የተውጣጡ 16 አባላትን የያዘ ሲሆን በየሳምንቱ አርብ በመገናኘት የተሠሩ ሥራዎችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን እና መሠራት የሚገባቸውን ተግባራት በጋራ ይገመግማል፤ የመፍትሔ አቅጣጫም ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መሠረት ያለመግባባት ችግር መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለይቶ ቅድሚያ የመምከርና የማስተካከል ስራ እየሠራ ለመማር ማስተማሩ ሥራ ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ አስገንዝቧል፡፡ በቀጣይም ፎረሙ ለግቢው ማህበረሰብ ልዩ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘዴዎች በመጠቀም ግንዛቤ ለመፍጠር እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተማሪ እሸቴ ምህረት ገልጿል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .