ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለህግ ተማሪዎች የብቃት ማረጋገጫ አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ሰጠ

  • -

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለህግ ተማሪዎች የብቃት ማረጋገጫ አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ሰጠ

Print Friendly, PDF & Email

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለህግ ተማሪዎች  የብቃት ማረጋገጫ አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ሰጠ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች  የመውጫ ፈተናውን በመውሰድ ላይ

 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ አመት የህግ ተማሪዎች የሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከታህሳስ 13 እስከ ታህሳስ 16/2013 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የመውጫ ፈተናውንም በአገር አቀፍ ደረጃ ከአራት ሽህ ተማሪዎች በላይ እንዲሁም በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ መቶ ሁለት ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ፈተናውን እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎችም በመደበኛው መርሃ- ግብር፣ በማታውና፣ ከዚህ በፈት ፈተናውን ወስደው ያላለፉ ተማሪዎች እንደሆኑም  ተጠቁሟል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ዲን አቶ ደጀኔ አላምረው እንደተናገሩት የመውጫ ፈተናው እንደ ሃገር የሚሰጥ መሆኑን አውስተው አላማውም የትምህርት ጥራቱን በማስጠበቅ በሃገሪቱ የሚታየውን  የፍትህ ስርአት ለማሻሻል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ስለሆንም ዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተናውን ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት መጀመሩን አስታውሰው አቶ ደጀኔ ዛሬም በመደበኛው መርሃ ግብር አርባ አንድ፣ በማታው መርሃ ግብር አርባ አራት እነዲሁም  በተለያዩ ምክንያቶች የቀሩ ሀያ አንድ የህግ ተማሪዎች  ፈተናውን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን  ተናግረዋል፡፡

አቶ ደጀኔ  አክለውም ተማሪዎቹ ከነበረው ሃገራዊ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝና ህግ የማስከበርን ዘመቻ ተከትሎ በተማሪዎች ላይ የሚፈጠረውን ስነ ልቦናዊ ጫና ለመቅረፍ ተማሪዎች ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት ስልጠናዎች እንደተሰጧቸውም ገልጸዋል፡፡

የሀገር አቀፍ የትምህርትና ምዘና ፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተናዎች  አስተዳድር ባለሙያ እና የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰብስቤ እንዲሪስ በበኩላቸው  እንደተናገሩት መውጫ ፈተና ማለት ተማሪዎቹ የተማሩትን የተግባርና ንድፈ ሃሳብ ትምህርት ምን ያህል እንደወቁት ለመመዘን የሚዘጋጅ ነው፡፡

አቶ እንድሪስ አክለው እንደገለጹትም ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተናውን  እንዲወስዱ የሚደረግበት ምክንያትም በሃገሪቱ ካለው የህግ ባለሙያ አቅም ማነስ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩትን የፍትህ ስርዓትና ክፍተት ለመሙላት ድርሻው የላቀ መሆኑን አውስተው ተማሪዎቹ  እራሳቸውን በማብቃት የተሻለና ተወዳዳሪ ሆነው ለፍትህ ስርዓቱ ዘብ የሚቆሙ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .