ለተማሪዎች አለመረጋጋት መንስኤ ለሚሆኑ ጉዳዮች መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ

  • -

ለተማሪዎች አለመረጋጋት መንስኤ ለሚሆኑ ጉዳዮች መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በታህሳስ ወር ተከሰቶ የነበረው የተማሪዎች አለመረጋጋት ሙሉ በሙሉ ወደ ሠላም መመለሡና ወደፊት እንዳይከሠት መንስኤ ለሚሆኑ ጉዳዮች መፍትሔ መስጠት ተገቢ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት አቶ ታደሠ ጤናው በዩኒቨርሲቲው ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት የመማር ማስተማሩ ሥራ ለ3 ተከታታይ ቀናት ተቋርጦ እንደነበር በማስታወስ ለአለመረጋጋቱ ምክንያትም በዋናነት በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተከሠተውን ችግር የዩኒቨርሲቲው አመራር አካላትና መምህራን ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ወደ ነበረበት ሁኔታ የመመለስ ስራ ሰርተዋል፡፡ እንዲሁም የተማሪዎች ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡

አቶ ታደሰ ጤናው አያይዘውም የተረጋጋ ሠላም አለመኖሩ ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጫና ከመፍጠር ባሻገር ለትምህርት ጥራቱም ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነና የተቋረጡት የትምህርት ቀናት በማኔጅመንት በመወሠን መምህራን በማካካሻ ፕሮግራም እንዲያካክሱ ከማድረግ በተጨማሪም የትምህርት ካሌንደሩን በመከለስ እንዲስተካከል የማድረግ ሥራ እንደተሠራ ገልፀዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተቋማዊ ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አባትሁን አለኸኝ በበኩላቸው ሠላም ባለመኖሩ ምክንያት ተማሪዎች የስነልቦና አለመረጋጋት፤ ለመማር ዝግጁ አለመሆን፣ ወደ ክፍል አለመግባት እና ተረጋግቶ አለማንበብ ተከስቶ እንደነበር በዚህ ደግሞ ኮርሶች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እንዳይሸፈኑ ስለሚያደርግ በት/ት ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው አብራርተዋል፡፡ ስለዚህ የትምህርት ካሌንደር ተከልሶ ከነበረው የ4 ቀናት ጭማሬ ተደርጐ ኮርሶች እንዲሸፈኑ እንደተደረገ እና መምህራን በየትምህር ክፍሎች ተማሪዎችን የመምከርና የማረጋጋት ሥራ መስራታቸውን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ወደፊት እንደነዚህ አይነት ችግሮች እንዳይፈፀሙ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች እና የማስገንዘብ ስራ መሥራት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .