ለ200 የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገለፀ

  • -

ለ200 የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገለፀ

Print Friendly, PDF & Email

ደ/ማ/ዩ፡- በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ላሉ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው 200 ተማሪዎች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገለፀ፡፡ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ-ፆታ፤ ኤች አይ ቪ/ኤድስና አካል ጉዳተኞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ወ/ሮ የውልሰው መላክ የስራ ክፍሉ በዋናነት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር፤ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠትና ድጋፍ በማድረግ በኩል በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህ አመትም የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው አካል ጉዳተኞች፤ ኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው እንዲሁም ወላጆቻቸውን ያጡና ረዳት የሌላቸው ተማሪዎች የገንዘብ፤ የቁሳቁስና የኮፒ አገልግሎት ድጋፍ እንዲያገኙ የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ድጋፉም የሚገኘው ከፓስ ፋይንደር፤ ከሲቪኤም ኢትዮጵያ እና ከዳይሬክቶሬቱ የውስጥ ገቢ ነው፡፡ ዳይሬክቶሬቱ የውስጥ ገቢውን ለማጠናከር ስምንት ኮንቴነሮችና አምስት ፑሎችን ግቢው ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ስራ ሰርቷል፡፡

ወ/ሮ የውልሰው አያይዘውም ለነዚህ ተማሪዎች ድጋፍ መደረጉ ትምህርታቸውን ተረጋግተው እንዲማሩ፤ የሚደርስባቸውን የስነ ልቦና ጫና እንዲቀንስና ወደ አልባሌ ቦታ እንዳይሄዱ ያደረገ ሲሆን በትምህርት ውጤታቸውም መሻሻል እንዳሳዩ አብራርተዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በበኩላቸው ድጋፍ በማግኘታቸው የትምህርት ቁሳቁስ፤ የጤናና የንፅህና ቁሳቁስ ማሟላት እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከልዩ ልዩ የስነ ልቦና ጫና መላቀቅ በመቻላቸው የትምህርት ውጤታቸው መሻሻሉን ገልፀው በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ ተማሪዎች ይህን መሰል ድጋፍ እንዲያገኙ ቢደረግ በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .