ታሪክን ከትውልድ ትውልድ ለማስተላለፍ ወላጆች፣ ምሁራንና መንግስት ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ተባለ

  • -

ታሪክን ከትውልድ ትውልድ ለማስተላለፍ ወላጆች፣ ምሁራንና መንግስት ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ተባለ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደ/ማ/ዩ፡- የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 77ኛውን የድል ቀን ምክንያት በማድረግ ዓውደ ጥናት አካሄደ፡፡ ሚያዝያ 27 ቀን ሲታሰብ ሁሌም የሚያዚያ 27/1928 ኢትዮጵያ የተወረረችበት እና ሚያዚያ 27 ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት ትግል በኋላ ድል ያደረገችበት ስለሆነ የመከራና የድል ቀን ሆኖ ይታሰባል፡፡

አውደ ጥናቱ ታዋቂ የታሪክ ምሁራን፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር በለጠ ያዕቆብ ጀግኖች አርበኞች የጣሊያንን ጦር ኋላቀር በሆነ መሳሪያ የተዋጉ ቢሆንም የነበራቸው የአልሸነፍ ባይነት ወኔ ለድል እንዳበቃቸው በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ከአምስት አመታት እልህ አስጨራሽ ጦርነት በኋላ በ1933 ዓ.ም. የጠላትን ጦር ሙሉ በሙሉ በማስወጣት የነፃነት ተምሳሌት የሆነውን የኢትዮጵያን ባንዲራ በአዲስ አበባ መስቀል መቻላቸውን በማስታወስ በዕለቱ የተከበረው በዓልም የጥንታዊ የሀገራችን አርበኞች የጽናት፤ የነፃነት እና የሀገር ወዳድነት ተምሳሌት መሆናቸውን ለማስታወስና ጠንካራ ታሪካቸውን ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በማሠብ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ሰለጠነ ስዩም “የጐጃም አርበኞች ተጋድሎ” በሚለው ጽሁፋቸው የጣሊያንን ጨካኝና አረመኔ ጦር ከሀገር ለማስወጣት ሽፍትነት፤ የመንግስት ሠራተኞች፣ የቀድሞ ወታደሮች እና ህዝቡ ዋና የትግል ምንጭ በመሆን እንዳገለገለ በዚያም በመላ ሀገሪቱ በተለይም ደግሞ በጐጃም ትግሉ እየተጠናከረ እንደመጣና የጠላት ጦር መቋቋም እንዳቃተው አስታውሠዋል፡፡

የገጠር አርሶ አደር አርበኞች ለጠላት አስቸጋሪ እንደነበሩና ጠላትን በማስጨነቅ የሀገራቸውን ነፃነት በማስጠበቅ ባለ ታሪክ እንደሆኑ እና የአሁኑ ትውልድ ከአርበኛ አባቶች ጽናትን፣ ትዕግስትን እና ጥንካሬን መማር እንዳለበት ዶክተር ሰለጠነ ገልፀዋል፡፡

ሌላኛው አርበኞችን አስመልክቶ የጥናት ጽሁፍ ያቀረበ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው የአርበኞችን ተጋድሎ በዝርዝር ካስቀመጡ በኋላ የአርበኞችን ጥንካሬ እና የነፃነት ተምሳሌት ከትውልድ ትውልድ ለማስተላለፍ ወላጆች፣ ምሁራንና መንግስት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውና ወጣቶች የአባቶቻቸውን ታሪክ እንዲያውቁ እንዲሁም ለሀገራቸው ሁለንተናዊ እድገት ወሣኝ ተሣትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በበዓሉ የተገኙት ፕ/ር ሹመት ሲሻኝና ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ አርበኝነት በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ሲያልፍ ልጅ የአባቱን ታሪክ እያጠፋ የራሱን የሚፅፍበት ጊዜ ማብቃት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .