የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የአመራሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተነገረ

  • -

የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የአመራሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተነገረ

Print Friendly, PDF & Email

ደ/ማ/ዩ፡- የምስ/ጐጃም ፣ የምዕ/ጐጃም እና የአዊ ዞኖች የትምህርት አመራሮች የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል የፓናል ውይይት አካሄዱ፡፡ ውይይቱ ከትምህርት ጥራት ስኬት አንፃር የአመራሮች ሚና ምን ይመስላል በሚል ርዕሠ ጉዳይ በፍኖተ-ሠላም ከተማ ከየካቲት    23-25/2ዐ1ዐ ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

ዶ/ር በለጠ ያዕቆብ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ኤክዝኪዩቲቭ ዳይሬክተር በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በሀገራችን የትምህርት ደረጃዎች እየጨመረ በአንፃሩ ግን የትምህርት ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ በዚህም ረገድ ብቁ ዜጋ፣ የተስተካከለ አመለካከት ክህሎትና እውቀት፣ የሀገሪቱንም ለውጥ ተሸክሞ የማህበረሰቡን ፈጣን ለውጥ እና እድገት ማምጣት የማይችሉ ዜጐችን መመለከት እየተለመደ እንደመጣ ተናግረዋለ፡፡ስለሆነም በዞን ፣ በወረዳና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የትምህርት አመራሮች በጋራ በመተባበር ለት/ት ጥራት አልመውና ከመቼውም በላይ ሊሠሩ እንደሚገባ ዶ/ር በለጠ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሆን ለተለያዩ የስራ መስኮች ብቁ፣ ጠንካራ ተወዳዳሪ ሥራ ፈጣሪ ዜጋን መፍጠር እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

ስለሆነም የትምህርት አመራሩ በሁሉም በተለየ ችግሩን በየደረጃው በመለየት፣የራሱን ድርሻ በመውሠድ፣ ውስብስብ የሆነውን የማህበረሰቡን ችግር ቀድሞ በመረዳትና ተገቢ ምላሽ በመስጠት ቀጥተኛ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ በትኩረትና በምክንያታዊነት ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አቶ ገበየሁ ሽፈራው እና አቶ እሸቱ ክብረት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስነ-ትምህርት፣ ስነ-ባህሪ ተቋም መምህር በትምህርት አመራሮች የሚስተዋሉ መልካም ተሞክሮዎች እና ተግዳሮቶችን አቅርበው የፓናል ውይይት ተደርጐበታል፡፡ የትምህርት ጥራት ውድቀት፣ የአመራሮች ሚና በትምህርት ትራት ላይ አመራርነት፣ የርዕሳነ-መምህራንና ባለድርሻ አካላት በትምህርት ጥራት ላይ ያላቸው ሚና ለትምህርት ጥራት ተጠቃሽ መልካም አጋጣሚዎች፣ ተግዳሮቶች እና ሌሎችንም በስፋት የዳሠሠ እንደነበር ከጽሁፉ ተገንዝበናል፡፡

ከዞን ትምህርት መምሪያ፣ ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት፣ በየዞኑ ከሚገኙ ሁለተገኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን እና የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የትምህርት አመራሮች በውይይታቸው በተቋማትና በባለድርሻ አካላት መካከል የመገፋፋትና ጤና ያልሆነ ፉክክር መኖር፣ የትምህርት ስርዓቱ በንድፈ ሐሳብ ብቻ የተሞላበት መሆን፣ በብቃትና በቁርጠኝነት ስራዎችን አለመስራት፣ የትምህርት ስራን በዘመቻ መስራትና ወቅታዊ ብቻ ማድረግ፣ የተማሪና የመምህራን የስነ-ምግባር ችግር መታየት፣ በአመራርነት የሚወጡ አመራሮች በተገቢው መንገድ ተመልምለው ያለመምጣት፣ ሙያን በተጠያቂነትና በብቃት ያለመስራት፣ የወላጆች ለልጆቻቸው የሚሠጡት ትኩረትና ክትትል አናሳ መሆን እና የመሣሠሉት ለትምህርት ጥራት ውድቀት ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ታደሠ ጤናው በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካ/ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት በውይይቱ ተገኝተው እንደተናገሩት የትምህርት ጥራት በዋናነነት በግብዓት፣ በሂደትና በውጤት የሚመዘን ቢሆንም ይህንን አስተሳስሮ በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ሊመራ የሚችል የትምህርት አመራር እንደሚያስፈልግ በመግለጽ የትምህርት አመራሮች በተለይ የትምህርት ግብዓቶችን በዕቅድ በመምራት የተማሪን ዲስፕሊን በጥብቅ ለመቆጣጠር፣ የኩረጃን ባህል በጽኑ በመቃወም፣ የወላጅ ት/ቤት ግንኙነትን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል፣ መምህራን በስልጠናና በልምድ ልውውጥ ተሞክሮአቸውን ለማሳደግ፣ ከተለያዩ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠርና በመረዳዳት ብቁ፣ ስራ ፈጣሪና አገር ተረካቢ ትውልድ ልንፈጥር ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .