የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

  • -

የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

Print Friendly, PDF & Email

ደ/ማ/ዩ፡- የኤች አይቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከመንግስታዊ፤ መንግስታዊ ያልሆኑ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ እና የተማሪዎች ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጋር የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ-ፆታ፤ ኤች አይ ቪ ኤድስና አካል ጉዳተኞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የውልሰው መላክ ዳይሬክቶሬቱ ለተማሪዎቹ ምቹ የመማር ሁኔታ በመፍጠር በተለይም ደግሞ የስነ-ተዋልዶ ጤና ሁኔታዎችን በማሻሻል ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ልዩ ልዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከተከናወኑ ተግባራት መካከልም የህይወት ክህሎት፤ የስነ-ተዋልዶ ጤና፤ የኮንዶም ስርጭት፤ የእህቶች ለእህቶች፤ የአቻ ለአቻ ውይይት እና ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አስተማሪ ፖስተሮች፤ ብሮሸሮች እና ቢልቦርዶች ተዘጋጅተው ግንዛቤ እንዲፈጠር የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከመንግስት አካላት፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ ከክበባት፤ ከተማሪዎች አደረጃጀቶችና ከውጭው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት የኤች አይ ቪ/ ኤድስን ስርጭት የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ መሆኑን በማስረዳት በግቢው ውስጥ የተሰጡ ስልጠናዎች የፆታዊ ትንኮሳን በመቀነስ፤ የጓደኛ ተፅዕኖን በመቋቋም፤ በራስ መተማመን በመጨመር እና ላልተፈለገ እርግዝና ተጋላጭነት መቀነስ የታዩ ለውጦች እንደሆኑ በሚደረጉ ውይይቶች ማወቅ ተችሏል፡፡ በቀጣይም የመጣውን ለውጥ በጥናት የተደገፈ ለማድረግ ልዩ ልዩ ትልመ ጥናቶች እንዲሰሩ ተደርጎ የተሻለውን በመምረጥ ወደ ስራ እንዲገባ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ድጋፎች የተደረገላቸውና ስልጠናውን ያገኙ ተማሪዎች በበኩላቸው አቅማቸውን ሊያጎለብቱ የሚችሉ ስልጠናዎችን ያገኙ በመሆኑ የአቻ ግፊትን በመቋቋም፤ ከአጋላጭ ባህሪያት ራሳቸውን ማራቅ እንደቻሉ በመናገር የሚሰሩ ስራዎች ግን በቂ እንዳልሆኑና ከዚህ የበለጠ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .