የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም በቀረቡ ሰነዶች ላይ የውይይት መድረክ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም በቀረቡ ሰነዶች ላይ የውይይት መድረክ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

Print Friendly, PDF & Email

 

ደማዩ ህዳር 22/2013ዓ/ም፡- የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ፣ ባህልና ስነ-ጽሁፍ የልህቀት ማዕከል ማቋቋሚያ ሰነዶች ላይ የውይይት መድረክ በዩኒቨርሲቲ ተክለ ኢየሱስ ዋቅጅራ አዳራሽ ህዳር 22/2013 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ በውይይት መድረኩም የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ዲኖች ፣ዳይሬክተሮችና መምህራን ተሳትፈውበታል፡፡

  የየዩኒቨርሲቲው ስነ-ጽሁፍ መምህርና የአቋቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ደመቀ ጣሰው የመወያያ ሰነዱን ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን የልህቀት ማዕከሉ ዋና አላማም  የባህል፣ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ የልህቀት ማዕከል በደብረ ማርቆስና አካባቢው ያለውን ሀብት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ በማዋል ህብረተሰቡ ወቅቱን የዋጀ ሁለንተናዊ እድገት ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሆነ  ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ደመቀ አክለው  እንደገለጹት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢዉን የባህል፣ ቋንቋና ስነ-ጽሁፍ እምቅ ሃብት የተረዳ ተቋም መሆኑን አውስተው ይህንንም ሃብት ለማልማት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከናዉን  መቆየቱንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡ እስካሁን የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም በእነዚህ ዘርፎች ከዚህ በላይ ለመስራት የልህቀት ማዕከል ማቋቋም አስፈላጊነቱ ታምኖበት ወደ ስራ  መገባቱን ተናግረዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በግብርናና ሰብል ልማት፣ በቋንቋ፣ በስነ-ጽሁፍና ባህል ላይ የልህቀት ማዕከሉን በማድረግ አስር አመት የተቋሙን ስልታዊ እቅድ መንደፉ ይታወቃል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .