የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻው የስንቅ ዝግጅት አደረጉ

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻው የስንቅ ዝግጅት አደረጉ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደ/ማ/ዩ፡- በአገራችን ላይ በትህነግ የተከፈተብንን ወረራና ጭፍጨፋ ለመመከት ግንባር ላይ እየተዋደቁ ለሚገኙ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል፣ ለሚሊሻና ፋኖ በሚደረገው የስንቅ ዝግጅት ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ እና የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መንበሩ ዘውዴ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡  

በጉብኝቱም በስንቅ ዝግጅቱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞችን አበረታተዋል፡፡ የስንቅ ዝግጅቱ የህልውና ዘመቻው እስከሚጠናቀቅ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መልዕክት አስተላለፈዋል፡፡

በስንቅ ዝግጅቱ ላይ የነበረው ከፊል ገጽታ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንትና የስንቅ ዝግጅት አስተባባሪ ዶክተር አስካለማርያም አዳሙ በበኩላቸው  የአሸባሪ ቡድኑ፡- እንደ ምሁር እንዳናስብ፣ እንዳናስተምርና እንዳንመራመር በርካታ በደሎችን ሲፈጽምብን መቆየቱ ሳንወድ በግድ ጦርነቱን እንድንቀላቀል እንዳደረገንና ይህንን አሸባሪ የሃገር ጠላት ቡድን ሁሉም ዜጋ ሴት ወንድ ሳንል አንድ በመሆን ሃብት በማሰባሰብ፣ ማህበረሰቡን በማንቃትና በጦር ግንባር ለሚገኘው ሰራዊት የስንቅ ዝግጅት በማቅረብ አለኝታነታችንን ልናሳይና የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ መቀልበስ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ዶክተር አስካለማርያም አዳሙ

የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንትና የስንቅ ዝግጅት አስተባባሪ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሳቸው ሽታው ደግሞ ምሁራን ካሁን በፊት እውቀታቸውን፣ ልምዳቸውንና ተሞክሯቸውን በመቀመር ለማህበረሰቡ ማካፈል ነበር አሁን ግን ሳንፈለግ ተገደን ወደ ጦርነት ገብተናል፤ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለአንድ ዓላማ በመሰለፍ ይህን ወራሪ ኃይል መመከት ያስፈልጋል፤ ጎን ለጎን  እያንዳንዱ የየራሱን ስራ መስራት ያለበት ሲሆን ግንባር ላይ እየተፋለሙ ለሚገኙ ወገኖቻች የስንቅ ዝግጅቱን በማጠናከር ቦታው ደረስ ማድረስ፤ እስከ ግንባር በመዝመት ይህን አሸባሪ ቡድን ድል ማድረግና ግንባር ላይ እየተዋደቁ የሚገኙ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብላቸውን በመሰብሰብና  የሚያስፈልጋቸዉን ሁሉ በማገዝ  አላፊነታችንን መወጣት አለብን  ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ መምህርና የስንቅና ሎጅስቲክ አሰባሳቢ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ደረጀ አደመ እንደገለጹት በስንቅ ዝግጅቱ ላይ ደረቅ ምግቦች፡- እንደ ቆሎ፣ ዳቦ ቆሎ እና የውሃ የመሳሰሉት ዝግጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በስንቅ ዝግጅት ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ መምህር  አቶ ባንታየሁ ታምሬ በአስተያየታቸው ያለንበት ወቅት ክልላችን ብሎም ሃገራችን በትህነግ አሸባሪ ኀይል ተወሮ ይገኛል፤ በዚህም በርካታ የክልላችን ህዝቦች ተጨፍጭፈዋል፤ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈዋል፤ ስለዚህ ወረራውን ለመመከት የክልላችን ልዩ ኀይል፣ ፋኖና ሚሊሻ እንዲሁም አርሶአደሮች በቦታው እየተፋለሙ ስለሚገኙ ከጎናቸው በመቆም እንደሚገባ በመግለጽ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል፡፡

በመጨረሻም ጦርነቱን ድል እስከምናደርግ ድረስ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በወጣለት መርሃ-ግብር መሰረት የስንቅ ዝግጅቱን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የስንቅ ዝግጅት አስተባባዎች  ማሳሰቢያ ሰጠዋል፡፡

       የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስንቅ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .