የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በ2012 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በ2012 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

Print Friendly, PDF & Email

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአሰርተዳደር ሰራተኞች የ2012 በጀት አመት ዕቅድን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመፈጸም በእቅዱ ሊካተቱ ስለሚገባቸው ጉዳዮችና ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰሩ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በዩኒቨርሲቲው ዮፍታሄ ንጉሴ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የአንድ ቀን ውይይት አካሄዱ፡፡

በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የእቅድ ዝግጅግት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ ፣ አቶ አክሊሉ ጌታቸው ለዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችየ2012 ዓ.ም ዕቅድን  ሲያስተዋውቁ

የደብረ ማረቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም እቅድ ፣ የ2011 በጀት አመት እቅድ  አፈጻጸምና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች ፣የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን  እቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች፣አምስተኛው የትምህርት ሴክተር ልማት ፕሮግራም  እቅድ፣ የዩኒቨርሲቲው  የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ፣ የትምህርት ሚኒስቴር የ2012 በጀት አመት ጠቋሚ እቅድና የዩኒቨርሲቲው ሌጅስሌሽንን መነሻዎች  በማድረግ  በየደረጃው  የለውጥ ፕሮግራሞችን  ተግባራዊ  በማድረግ ፣ እቅዱን በተሟላ መልኩ  በመተግበርና የክትትል ፣ግምገማና ድጋፍ ስርአትን  በማጎልበት የትምህርት  ጥራትን  ማረጋገጥ የእቅዱ ዓላማ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በእቅድ ትውውቁ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት  ዶክተር ታፈረ መላኩ  እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በ2012  በጀት አመት  በርካታ ተግባራትን  ለመፈጸም ያቀደ መሆኑን ገልጸው የዩኒቨርሲቲው  መምህራንና ሰራተኞች በእቅድ ትውውቁ ያሳዩት የስራ ተነሳሽነትና የመለወጥ መንፈስ ትልቅ በመሆኑ በዚህ መንፈስ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ወደ ስራ መሰማራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

የየክፍሉ ሀላፊዎችም ከሰራተኞች ጋር ውይይት በማድረግ  ውጤታማ ስራ ለመስራት  የሰራተኞችን ተነሳሽነት  መጠቀም  እንደሚገባ  ገልጸዋል፡፡ በ2012 የተሻለ የስራ አፈጻጸም ያለቸውን መምህራንና ሰርተኞችንም  ለማበረታታት  በእቅዱ ማትጊያ የተካተተ መሆኑም ለማወቅ ተችሏል፡፡ለዚህም የተሻለ የሰሩትን ለመለየት  ሁሉም መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በየክፍላቸው የተሻለ የሰራውን ለመምረጥ  ሳይቸገሩ  መረጃን መሰረት አድርገው ሊሆን  እንደሚገባው ዶ/ር ታፈረ  አሳስበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ያሉትን  ተግባራት ለማህበረሰቡ እውቅና ለመፍጠርም የኮሚዩኒኬሽን  ዘርፉን የተሻለ ለማድረግ  ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ  ዶ/ር ታፈረ አክለው ተናግረዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 2012 ዓ.ም እቅድ ዘጠኝ ግቦች ሲኖሩት  በግቦች ስር ያሉ አርባ ሁለት የአፈጻጸም መለኪያዎችን  በመጠቀም በየሩብ አመቱ የእቅድ አፈጻጸሙን የመለካትና ጠንካራ አፈጻጸሞችን የማጎልበት እንዲሁም ክፍተቶችን በልዩ ሁኔታ የማረም ስራ  በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡

በ2012 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ ውይይት ላይ መምህራንና ሰራተኞች እቅዱ ሊያሰራ የሚችልና ዩኒቨርሲቲውን ወደ ፊት ሊያራምደው የሚችል መሆኑን ገልጸው ለእቅዱ ስኬት ሁሉም ባለድረሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ጥረት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞችም በእቅዱ ሊካተቱ የሚገቡ ጉዳዮችን በመጠቆም  ጥያቄዎችን አንስተው  መልሶች ተሰጥተዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም የተሰጡትን ተልኮዎች ለመፈጸም 570,247,000.00 ብር መደበኛ በጀትና 540,000,000.00 ብር ካፒታል በጀት በድምሩ 1,110,247,000.00 ብር   ሆኖ ጸድቋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .