የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኤክስቴንሽን ተማሪዎች የጋራ መፀዳጃ ቤት ሰርተው አስረከቡ

  • -

የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኤክስቴንሽን ተማሪዎች የጋራ መፀዳጃ ቤት ሰርተው አስረከቡ

Print Friendly, PDF & Email

 

ደ/ማ/ዩ፡-የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኤክስቴንሽን ተማሪዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ በ3 ቦታዎች ላይ የጋራ መፀዳጃ ቤቶችን ሰርተው አስረከቡ፡፡

ተመራቂዎች ወደ ህብረተሰቡ በሚገቡበት ጊዜ ከህብረተሠቡ ጋር በቀላሉ ተግባብተው በማህበረሰቡ ውስጥ የተጋረጡትን ችግሮች በመለየትና ሳይንሳዊ ዘዴን ተጠቅመው ቅድሚያ በመስጠት ወደ ተግባር መግባት አንዱ የትምህርታቸው አካል እንደሆነ በመገንዘብ፣ የቤት ለቤት የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ግንዛቤ መፍጠር እና ሌሎች ተግባራትን መስራት እንደቻሉ ተማሪዎች ገልጧል ፡፡

በስራቸው ወቅት በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሟቸውም ጥሩ የተግባቦት መንፈስ በመፍጠር አንድነታቸውን ያጠናከሩበት፣ የቡድን ስራን ያሰፈኑበት ብሎም የህብረተሠቡን ችግር ለመቅረፍ ከህብረተሰቡ ጋር ተግባብተው መስራት የቻሉበት በድልም ኃላፊነታቸውን የተወጡበት እንደነበረ ተማሪዎች አስረድተዋል፡፡

በዚህም ረገድ በአየር ማረፊያና አካባቢው ለአሽከርካሪዎች፣ ለቆሎ ተማሪዎች ለግቢ ተማሪዎችና ለሌሎች ተጠቃሚዎች ሁለት ሽንት ቤት ሰርተው አስረክበዋል፡፡ በቀበሌ ዐ3 ደግሞ ለገበያተኛው የጋራ መጠቀሚያ የሚያገለግል ያስጀመሩት የጉድጓድ ቁፋሮ ስራ ከቀበሌዎች፣ ከአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ ከመንቆረር ኢንተርፕራይዝ /ኮንስትራክሽን/፣ ከአልማና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮጀክቶች መሰራታቸውን ተማሪዎች አብራርተዋል፡፡

በቀጣይም አዲስ የሚመደቡ የግልና የመንግስት ተማሪዎች የተጀመረውን የፕሮጀክት ስራ አጠናክረው በመስራት ከፍፃሜ እንዲያደርሱት ተመራቂ ተማሪዎች አሣስበዋል፡፡ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲም ከፍተኛ ሚና ሊኖረው እንደሚገባ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ታደሰ ጤናው እና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ገነት ደጉ ተማሪዎች ወደ ህብረተሰቡ ገብተው ስራቸውን በሚሠሩበት ጊዜ በርካታ ፈተና እንደገጠማቸውና በከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ችግሮችን መፍታት እንደቻሉ ልምድም እንዳገኙበት ገልፀዋል፡፡ ይህ ለቀጣይ ከማህበረሰቡ ጋር ለሚሠሩት ሥራቸው የተሻለ አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል፡፡ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተቻለው አቅም ሁሉ እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ዱቤ ጃራ በበኩላቸው የጤና ሳይንስ ኤክስቴንሽን ተማሪዎች በፅንሰ-ሃሳብ ደረጃ የተማሩትን እውቀት ወደ ማህበረሰቡ ሲገቡ በምን መልኩ መተግበር እንዳለባቸው የሚያሳይ የተግባር ትምህርት ሰርቶ ማሳያ ነው፡፡ ዓላማውም ተማሪዎች በሚመደቡበት ቦታ ሁሉ የሚገጥሟቸውን ችግሮች በቀላሉ ተረድተው ከመለየት ጀምሮ ህክምና እስከመስጠት ድረስ ያለውን ሂደት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ስራ እንደሠሩ ማስቻል ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም እነዚህን ተግባራት ዩኒቨርሲቲው በፕሮጀክት ቀረፆ መምህራን የሚገቡበት ሁኔታ ይመቻቻል ሲሉም አብራርተዋል ፡፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ የቀበሌ ዐ7 ምክትል አስተዳደር አቶ መከተ ተመስገን በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአካባቢያችን መፀዳጃ ቤት የህብረተሰቡ አንገብጋቢ ችግር መሆኑን ለይተው ችግሩን ለመቅረፍ በቀበሌ በሠሯቸው ተግባርም ተቀጥረው በሚሄድበት አካባቢ መልካም ስራ እንደሚሠሩ አመላካች ተግባር በመሆኑ ሊያስቀጥሉት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ከጐናቸው ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ጤና ጣቢያዎች የተበላሹ የማሽን ጥገና ስራዎችን በመስራት ከፍተኛ ወጭ የሚገመት ገንዘብም አድነዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .