የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች መመረቂያ ጽሁፎች የማህበረሠቡን ችግር ሊፈቱ በሚችል መልኩ መዘጋጀት እንዳለባቸው ተገለፀ

  • -

የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች መመረቂያ ጽሁፎች የማህበረሠቡን ችግር ሊፈቱ በሚችል መልኩ መዘጋጀት እንዳለባቸው ተገለፀ

Print Friendly, PDF & Email

 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 87 ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሁፋቸውን አቀረቡ፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አሐዱ መንዝር በአሁኑ ሠዓት በዩኒቨርሲቲው በ37 የትምህርት መስኮች 2913 የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በመደበኛው፣ በማታውና በክረምት መርሀ ግብሮች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልፀው በ9 የትምህርት መስኮች ከጥር ወር 2ዐ1ዐ ዓ.ም. የመመረቂያ ጽሁፋቸውን እንዲያቀርቡ የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመመረቂያ ጽሁፍ ዋና ዓላማ የማስተርስ ድግሪውን ለማግኘት በከፊል መስፈርት መሆኑ እና የአካባቢውን ማህበረሠብ ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ጥናቶች እንዲዘጋጁ ለማድረግ ሲሆን ሁሉም የሚሰሩ የምርምር ጽሁፎች በዚህ መልኩ መዘጋጀታቸውን የመከታተል እና ወደ ፕሮጀክት እንዲቀይሩ የማድረግ ክፍተት እንዳለ አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም የተማሪዎችን ሥራ በተገቢው መልኩ ሠንዶ በመያዝ ለማጣቀሻነት እንዲያገለግሉ የማድረግ ሥራ የሚፈለገውን ያህል ትኩረት ባይሠጠውም የተሻሉ ጽሁፎችን ግን በቤተ መጽሐፍት እንዲቀመጡ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ እንዲሁም ተማሪዎች ጥሩ መመረቂያ ጽሁፍ እንዲያዘጋጁ አንጋፋ መምህራንን በአማካሪነት በመመደብ የማገዝና የመደገፍ ሥራ በሠፊው እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወደፊትም የመመረቂያ ጽሁፎች በዩኒቨርስቲው የምርምር የትኩረት አቅጣጫ መሠረት እንዲዘጋጁ እና ከሌላ ሠው ሥራ ተቀድተው እንዳይቀርቡ ትኩረት ሠጥተው እንደሚሠሩ ጠቁመዋል፡፡

የጥናት ጽሁፍ ያቀረቡት ተመራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው የተመደቡላቸው አማካሪዎች ተገቢውን ድጋፍ ሲያደርጉላቸው እንደነበር በመግለጽ ያቀረቧቸውን ጽሁፎች የመጨረሻ ቅርጽ በማስያዝ እና ተጨማሪ ማስተካከያዎች በማድረግ የማሳተምና እውቅና እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው በአማካሪነት የሚመድባቸው መምህራን ተገቢውን እገዛ እንዲያደርጉ ክትትል የማድረግና መመረቂያ ጽሁፎች በደንብ ተሠንደው እንዲያዙ የማድረግ ስራ እንዲሠራ ጠቁመዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .